ከኡሙ ሰለማ ኡሙል ሙእሚኒን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁት...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኛ ላይ መሪዎች እንደሚሾሙና ከፊል ስራዎቻቸው ከሸሪዓ ጋር የተስማማ ስለሆነ መልካም እንደምንለውና፤ ከፊሉን ደግሞ ከሸሪዓ ጋር ስለሚፃረር እንደምናወግዘው ተናገሩ። ውግዝ ተግባሮቻቸ...
ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ለወደፊት የምታወግዟቸው ጉዳዮችና አድልዎ ይከሰታል!' ሶሐቦችም 'የአ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሙስሊሞችን ገንዘብና ሌሎችንም አለማዊ ጉዳዮች በማዳላት ሙስሊሞችን በርሱ ላይ ካላቸው መብት በመከልከል እንደፈለጉ የሚያወጡ መሪዎች በሙስሊሞች ላይ እንደሚሾሙ ተናገሩ። በነርሱ ላይ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኝ ሁሉም ሙስሊም ላይ የሚሸከመውና የሚጠብቀው ኃላፊነት እንዳለበት ተናገሩ። ኢማምና መሪ አላህ ባስጠበቃቸው ኃላፊነት እረኞች (ኃላፊዎች) ናቸው። በርሱ ላይም...
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቴ ውስጥ ይህንን ሲሉ ሰምቻለሁ: "አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር...
የሙስሊሞች ጉዳዮች ውስጥ በየትኛውም ትንሽም ይሁን ትልቅ ሹመት ፣ አጠቃላይም ይሁን ቁንፅል ሹመትን የተሾመ ከዚያም ለሙስሊሞች ሳይራራ ችግርን በነርሱ ላይ የሚያባብስባቸው የሆነን ሰው ሁሉ ላይ አላህ በሰራው ስራ ተመሳሳይ እሱንም ለችግር...
ከተሚም አድዳሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።" እኛም "ለማን ነው (የምንቆረቆረው)" አልናቸው...
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የኢስላም ሃይማኖት በኢኽላስና በእውነተኝነት ላይ የቆመ መሆኑን ተናገሩ። ይህም ሁሉም አማኝ የታዘዘውን አላህ ግዴታ ባደረገው መልኩ ምንም ሳያጓድልና ሳያታልል በተሟላ መልኩ እስኪፈፅም...

ከኡሙ ሰለማ ኡሙል ሙእሚኒን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁትንም የምታወግዙትንም ስራ ይሰራሉ። (የሚሰሩትን ውግዝ ስራ) የጠላ ሰው (ከወንጀል) ጠራ። ያወገዘም ሰው ሰላም ሆነ። ነገር ግን (የነሱን ውግዝ ተግባር) የወደደና የተከተለ (ወንጀል ውስጥ ወደቀ)" ሶሓቦችም "ታዲያ አንዋጋቸውምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም "ሶላትን እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም (እንዳትዋጓቸው!)" ብለው መለሱ።

ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ለወደፊት የምታወግዟቸው ጉዳዮችና አድልዎ ይከሰታል!' ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ያዙናል?' አሉ። እርሳቸውም 'በናንተ ላይ ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ። ለናንተ ያላችሁን ሐቅ ደግሞ ከአላህ ትጠይቃላችሁ።' አሉ።"

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ። በሰዎች ላይ የተሾመ መሪ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ወንድ በቤተሰቡ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ሴት ልጅ በቧሏ ቤትና በልጆቹ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ናት። ስለነርሱም ትጠየቃለች። ባሪያ በአለቃው ገንዘብ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለርሱም ይጠየቃል። አዋጅ! ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።"

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቴ ውስጥ ይህንን ሲሉ ሰምቻለሁ: "አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር የዳረገ እርሱንም የሚቸገር አድርገው ። ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና ለነሱ የራራን ለርሱም ራራለት።"

ከተሚም አድዳሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።" እኛም "ለማን ነው (የምንቆረቆረው)" አልናቸው። እሳቸውም "ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ።" አሉ።

የምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ ብላለች፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሀፉን ያወረደ ነው። ከእርሱ (ከመፅሀፉ) ግልጽ የሆኑ አንቀጾች አሉ። እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው። ሌሎችም ተመሳሳዮች አሉ። እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን በመፈለግና ማጣመምን በለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ። (ትክክለኛ) ፍቺውንም አላህ ብቻ እንጂ ሌላ አያውቀውም። በዕውቀትም የጠለቁት "በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው" ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም።} [ኣሉ ዒምራን: 7] ቀጥለው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ " እነዚያ ከቁርኣን የተመሳሰለውን የሚከተሉትን ከተመለከትሽ አላህ ተጠንቀቁዋቸው ብሎ የጠቀሳቸው እነሱ ናቸው።"

አቡ ሰዒድ አል'ኹድሪይ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ ፡- የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡- "ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።"

ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "በአላህ ድንበር ላይ በአግባቡ የቆሙና የርሱን ድንበር የሚተላለፉ ሰዎች ምሳሌ በመርከብ ላይ (ቦታ ለመምረጥ) እጣ እንደተጣጣሉ ሰዎች ምሳሌ ነው። (በእጣው መሰረት) ከፊሉን የመርከቡ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉን ደግሞ የታችኛው ክፍል ደረሰው። የመርከቡ ታችኛው ክፍል ያሉት ውሃ ለመጠጣት የፈለጉ ጊዜ ላይኛው ክፍል ባሉት በኩል ያልፉ ነበርና "እኛም (ውሃ ለማግኘት) ፋንታችንን መርከቡን ብንሸነቁርና ከኛ በላይ ያሉትን ባናውካቸው መልካም ነው።" ተባባሉ። ከላይ ያሉት የታችኞቹ ፍላጎታቸውን እንዲፈፅሙ ከተዋቸው ሁሉም ይጠፋሉ። እጃቸውን ከያዙ ደግሞ እነሱም ይድናሉ። ሁሉም ይድናሉ።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው። ወደ ጥመት የተጣራ ሰውም የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ወንጀል ይኖርበታል። ይህም (በርሱ ላይ የሚኖረው ወንጀል) ከወንጀሎቻቸው ምንም ሳይቀነስ ነው።"

ከአቡ መስዑድ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "መንገድ ተቋርጦብኛልና የምጓጓዝበት እንስሳ ይስጡኝ?" አላቸው። እሳቸውም "የለኝም!" አሉት። ሌላ ሰውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ መጓጓዣ የሚሰጠውን እጠቁመዋለሁ!" አለ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።" አሉ።

ከሰህል ቢን ሰዕድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የኸይበር ቀን እንዲህ አሉ: "ነገ ይህንን ባንዲራ አላህ በርሱ እጅ ድልን ለሚያጎናፅፍ፣ አላህና መልክተኛውን ለሚወድ፣ አላህና መልክተኛውም የሚወዱት ለሆነ ሰው እሰጠዋለሁ።" ሰዎችም ለማን ነው የሚሰጠው? በሚል ሌሊታቸውን ተጠምደውበት አደሩ። ሰዎችም ያነጉ ጊዜ ሁሉም ባንዲራው እንዲሰጠው ተስፋ በማድረግ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ማልደው ሄዱ። እርሳቸውም "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ የት አለ? አሉ። ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አይኑን አሞታል" ተባሉ። እርሳቸውም "ሰው ላኩበት!" አሏቸው። እርሱም ተይዞ መጣና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዓይኑ ላይ ተፉና ዱዓ አደረጉለት። እርሱም ከዚህ በፊት ምንም በሽታ እንዳልነበረበት ሆኖ ተፈወሰ። ባንዲራውንም ሰጡት። ዐሊይም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንደኛው አምሳያ እስኪሆኑ ድረስ ልዋጋቸውን?" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም አሉት: "ቀያቸው እስክትሰፍር ድረስ ተረጋግተህ ተጓዝ። ቀጥሎ ወደ እስልምና ጥራቸው። በነርሱ ላይ ግዴታ የሚሆንባቸውንም የአላህ ሐቅ ንገራቸው። በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።"

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።"