- ለሁሉም ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን መታዘዙ፤
- በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ የተቆርቋሪነት (ቅን/ ታማኝ) ደረጃ የላቀ መሆኑን፤
- የእስልምና ሃይማኖት እምነቶችን፣ ንግግሮችንና ተግባራቶችን ያጠቀለለ መሆኑን፤
- ከነሲሓ መካከል አንዱ ቅንነቱ ለተገባው አካል ከማታለል ነፍሳችንን ማፅዳትና ለሱ መልካምን መፈለግ ነው።
- መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ነገር በጥቅሉ አውስተው ከዚያም መዘርዘራቸው የሳቸውን የማስተማር ብቃታቸው ውበትን ይጠቁማል።
- ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለአላህ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ጀምረው ከዚያም ለመጽሐፉ ከዚያም ለመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዚያም ለሙስሊም መሪዎች ከዚያም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ማጠቃለላቸው የትኛውንም ነገር እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ጉዳይ ሊጀመር እንደሚገባው እንረዳለን።