ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከበደል አስጠነቀቁ። ከበደል መካከልም: ሰዎችን መበደል፣ ነፍስን መበደል፣ በአላህ ሐቅ ላይ በደል መፈፀም ይጠቀሳሉ። በደል ማለት ሁሉንም የሐቅ ባለቤቶችን ሐቃቸውን ከመስጠት መተው...
ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!'" አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: "ቀጥለውም...
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በወንጀል፣ በሽርክና ሰዎችን በመብታቸው በመበደል ላይ ከመዘውተር አስጠነቀቁ። ምክንያቱም አላህ በዳይን ያዘገየዋል፣ ያቆየዋል ፣ እድሜውንና ገንዘቡንም ያረዝምለታል። በቅጣትም አያቻኩለውም። ካልቶበተ ግፉ ስለበ...
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ አላህ እንዲህ አለ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል ከ...
መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን እንደወሰነ ከዚያም ለሚፅፉት ሁለት መላእክቶች እንዴት እንደሚፅፉት እንዳብራራ ገለፁ። መልካምን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ሰው ባይሰራትም እንኳ ለሱ አንድ ምንዳ...
ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ፡- " የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?"...
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት አብራሩ። እስልምናውን አሳምሮ፣ እውነተኛና ሙኽሊስ (ያጠራ) ሆኖ የሰለመ ሰው ከመስለሙ በፊት በሠራው ወንጀል አይጠየቅም። ወደ እስልምና ከገባ በኋላ ሙና...
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ በፊት አብዝተው ነፍስ የሚገድሉ፣ አብዝተው ዝሙት የሚሰሩ የነበሩ የሺርክ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና...
ከሙሽሪኮች የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። አብዝተው የገደሉና የዘሞቱ ነበሩ። ለነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: የምትጣራው ኢስላምና አስተምህሮቶቹ መልካ...

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና። ስስታምነት ደማቸውን እንዲያፈሱና ሐራም (ያልተፈቀደውን) እንደ ሐላል አድርገው እንዲቆጥሩ አነሳስቷቸዋልና።"

ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!'" አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: "ቀጥለውም {የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።} [ሁድ: 102] የሚለውን አነበቡ።"

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ አላህ እንዲህ አለ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል ከዚያም ይህንን አብራርቷል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጻፍለታል ። እሱ (ለመስራት) አስቧት ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም አልፎ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎች ይጻፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጻፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።"

ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ፡- " የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል። "

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ በፊት አብዝተው ነፍስ የሚገድሉ፣ አብዝተው ዝሙት የሚሰሩ የነበሩ የሺርክ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ በመምጣት እንዲህ አሉ ' የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?' {እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉት፤ የማያመነዝሩትም ናቸው።} [ፉርቃን:68] የሚለውና {በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ።»} [አዝዙመር: 53] የሚለው አንቀፅ ወረደች።"

ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ ዘመን በምፅዋት፣ ነፃ በማውጣትና ዝምድና በመቀጠል የምፈፅማቸው አምልኮዎች ነበሩ በእነሱ እመነዳለውን?" አልኳቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለው መለሱለት፦ "ካሳለፍከው መልካም ተግባር ጋር ነው የሰለምከው።"

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል። ካፊር ግን ለአላህ ብሎ በሠራው መልካም ሥራ ምክንያት በዱንያ እንዲበላ ይደረጋል። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ በአኺራ የሚመነዳበት መልካም ሥራ አይኖረውም።"

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: ‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ደመና ቢደርሱና ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን ሊሞላ በቀረበ ወንጀል እኔ ጋር ብትመጣ ከዚያም በኔ አንድንም ሳታጋራብኝ ብትገናኘኝ እኔም ምድርን ሊሞላ በቀረበ ምህረት ወዳንተ እመጣለሁ።›"»

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከላቀውና ከተከበረው ጌታቸው ባስተላለፉት (ሐዲሥ) እንዲህ አሉ "አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ! " የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም አሁንም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ! የፈለግከውን ስራ በርግጥ ላንተ ምሬሃለሁ።"

ከዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "እኔ ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድን ሐዲሥ የሰማሁ ጊዜ አላህ በዛ ሐዲሥ በሻው መንገድ የሚጠቅመኝ ሰው ነበርኩ፤ ከሶሐቦቻቸው መካከል አንድ ሰው ሐዲሥ የነገረኝ ጊዜ ታዲያ አስምለዋለሁ። ከማለልኝ አምነዋለሁ። አቡበከር ለኔ አንድ ሐዲሥ ነግሮኛል። አቡበከር የነገረኝም እውነት ነበር። አቡበከር እንዲህ አሉ: 'የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።› ቀጥለውም ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢዐቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት} [ኣሊ ዒምራን:135] '"

ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "አላህ ዐዘ ወጀል በቀን ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) በምሽት እጁን ይዘረጋል። በምሽት ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) ደግሞ በቀን እጁን ይዘረጋል። ይህም ፀሀይ በመግቢያዋ በኩል እስክትወጣ ድረስ ቀጣይ ነው።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል። እንዲህም ይላል 'ማን ነው የሚለምነኝ የምመልስለት? ማን ነው የሚጠይቀኝ ለርሱ የምሰጠው? ማን ነው ምህረትን ከኔ የሚፈልገው ለርሱ የምምረው?'"