- የኢስላም ትሩፋትና ልቅናውን እንረዳለን። ኢስላም ያለፈውን ወንጀል ያስምራል (ያወድማል)።
- አላህ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ስፋቱን፣ ምህረቱንና ይቅር ባይነቱን እንረዳለን።
- የሺርክን ክልክልነት፣ ያለ ህግ ነፍስን የመግደልን ክልክልነት፣ የዝሙትን ክልክልነት፣ እነዚህን ወንጀሎች የሚዳፈር ላይ የመጣውንም ዛቻ እንረዳለን።
- ከኢኽላስና መልካም ስራ ጋር የተቆራኘ እውነተኛ ተውበት በአላህ መካድንም ጨምሮ ሁሉንም ትላልቅ ወንጀሎች ያስምራል።
- ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።