/ አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል

አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል። ካፊር ግን ለአላህ ብሎ በሠራው መልካም ሥራ ምክንያት በዱንያ እንዲበላ ይደረጋል። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ በአኺራ የሚመነዳበት መልካም ሥራ አይኖረውም።"
ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አላህ በአማኞች ላይ የዋለውን ትልቅ ችሮታና ከከሀዲያን ጋር ያለውን ፍትሀዊነት ያብራራሉ። አማኝ የሆነ ሰው የመልካም ሥራው ምንዳ ምንም አትጎድልም። በአኺራ ከሚደለብለት (ከሚከማችለት) ምንዳ በተጨማሪ በዱንያም በአምልኮው ምክንያት መልካምን ይሰጠዋል። ይህ ካልሆነ እንኳ ሁሉም ምንዳው ለሱ አኺራ ላይ ይጠበቅለታል። ካፊር ግን ለሠራው መልካም ሥራ የሚመነዳው በዱንያ አላህ በሚሰጠው መልካም ነገር ነው። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ ምንም የሚመነዳው ክፍያ አይኖረውም። ምክንያቱም በመልካም ሥራ በሁለቱም ዓለም ለመጠቀም የግድ ባለቤቱ አማኝ መሆን ይጠበቅበታል።

Hadeeth benefits

  1. በክህደት ላይ የሞተ ሰው ምንም ተግባር አይጠቅመውም።