ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: -ኑዕማን (መስማቱን ለማረጋገጥ) በሁለት ጣቶቹ ወደ ጆሮዎቹ እየጠቆመ፦ "ሐላል...
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነገሮች ሁሉ የሚያገለግል አጠቃላይ መርህን እያብራሩ ነው። ነገሮች ሁሉ በሸሪዐ መሰረት ወደ ሶስት ክፍሎች ይከፈላሉ: ግልፅ ሐላል ፣ ግልፅ ሐራምና ከፍቁድነትና ክልክልነት አንፃር ብዙ ሰው ብይናቸውን የማያው...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከና...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦችን ከመሳደብ ከለከሉ። በተለይ የመጀመሪያ ቀዳሚ የሆኑትን ሙሃጂሮችና አንሷሮችን መሳደብን ከለከሉ። ከሰዎች መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ የሚያህል ወርቅ...
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: አንድ እለት ከአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኋላ ሳለሁ እንዲህ አሉኝ "አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁኝ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል...
ኢብኑ ዓባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ህፃን እንደነበሩና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር እየጋለበ ሳለ ለሱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ እንዳሏቸው ይነግሩናል : እኔ አላህ በሷ የሚጠቅምህን ነገሮችንና ጉዳዮ...
ከሱፍያን ቢን ዐብደላህ አሥሠቀፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር...
ሶሐቢዩ ሱፍያን ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ‐ ስለርሱ አንድንም ሳይጠይቅ እርሱን አጥብቆ የሚይዘው የሆነን የኢስላምን ሀሳቦች የጠቀለለ የሆነን ንግግር እንዲያስተምሩት ነቢዩን (የአላህ ሶላትና...
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደድ፣ ከማዘን፣ ከመርዳት፣ ከማገዝና እነርሱ ላይ በሚደርስ ጉዳት አብሮ ከመጎዳት አንፃር ሙስሊሞች ከፊሉ ለከፊሉ ሊኖረው የሚገባውን ሁኔታ ልክ እንደ አንድ ሰውነት ምሳሌ ሊሆን...

ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: -ኑዕማን (መስማቱን ለማረጋገጥ) በሁለት ጣቶቹ ወደ ጆሮዎቹ እየጠቆመ፦ "ሐላል (የተፈቀደ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱንና ክብሩን ጠብቋል። አሻሚ ጉዳዮች ላይ የወደቀም ሰው ሐራም ላይ ወድቋል። የዚህ ሰው አምሳያ ልክ የተከለከለ ክልል ወሰን ዙሪያ እንደሚጠብቅና እንስሳዎቹም ወሰን አልፈው የሰው እርሻ ሊገቡ እንደቀረቡበት እረኛ ነው። አዋጅ! ለሁሉም ንጉስ ወሰን (ድንበር) አለው። አዋጅ! የአላህ ወሰን (ድንበር) ደግሞ ክልከላው ነው። አዋጅ! ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ከተስተካከለች ሁሉም ሰውነት ይስተካከላል። እሷ ከተበላሸች ደግሞ ሁሉም ሰውነት ይበላሻል። አዋጅ! እሷም ልብ ናት።"

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።"»

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: አንድ እለት ከአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኋላ ሳለሁ እንዲህ አሉኝ "አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁኝ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል፤ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ! እወቅ! ህዝብ ባጠቃላይ በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር ካልሆነ በስተቀር አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ለአንተ ፅፎብህ ካልሆነ በስተቀር አይጎዱህም። ብእሮቹም ተነስተዋል ጽሑፉም ደርቋል።"

ከሱፍያን ቢን ዐብደላህ አሥሠቀፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ"

ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት ይሰቃያል።"

ከዑሥማን ቢን ዐፋን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «አንድ ሰው የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ በባህር እንሳፈራለን፣ ከኛ ጋርም የተወሰነ ውሃ እንሰንቃለን። በዚህ በያዝነው ውሃ ዉዱእ ብናደርግበት እንጠማለንና በባህር ውሃ ዉዹእ እናድርግን?" የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት መለሱ: "እርሱ ውሃው አፅጂ ነው፤ ውስጡ የሞተም ሐላል ነው።"»

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንስሶችና አውሬዎች ተመላልሰው ስለሚጠጡት ውሃ ተጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ውሃው ሁለት 'ቁለተይን' ከደረሰ ነጃሳን አይሸከምም።"»

ከአቡ አዩብ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ" አቡ አዩብ እንዲህ አለ "ሻም ስንገባ ወደ ቂብላ አቅጣጫ የተገነባ መፀዳጃ ቤት አገኘን። ትንሽ ዘንበል እያልን እየተፀዳዳን አላህንም ምህረት እንጠይቀዋለን።"

ከአቡ ቀታዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።"

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዹእ ያደርጉ ነበር።"