- ህፃናትና ትናንሽ ልጆችን እንደ ተውሒድ፣ አዳቦችና ሌሎችንም የዲን ጉዳዮችን የማስተማር አንገብጋቢነት ፤
- ምንዳ በስራው አይነት እንደሆነ ፤
- ከሱ ውጪ ያለን ሁሉ በመተው በአላህ ላይ ብቻ መደገፍና በሱ ላይ ብቻ መመካት መታዘዙን ፤ እሱስ ምንኛ ያማረ መመኪያ ነው!
- በአላህ ውሳኔና ፍርድ ማመንና በፍርዱ መውደድ እንዳለብን ፤ አላህ ሁሉንም ነገር ወስኗልና።
- የአላህን መመርያ የጣሰ ሰው አላህ ያጠፋዋል እንጂ እንደማይጠብቀው ተምረናል።