- ውዱእን ሱናዎቹንና አዳቦቹን ተምሮ በመተግበር ላይ ትኩረት እንድናደርግ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- የውዱእን ትሩፋት እንረዳለን። ውዱእ ትናንሽ ወንጀሎችን የሚያስምር ነው። ትላልቅ ወንጀሎች ግን የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።
- ወንጀሎች ከሰውነታችን እንዲወጡ ውዱእን ማሟላቱና ያለምንም ጉድለት ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደገለፁት መፈፀሙ መስፈርት ነው።
- እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ወንጀሎችን ማስማር ትላልቅ ወንጀሎችን በመራቅና ከርሱ ተውበት በማድረግ ላይ የተገደበ ነው። አላህ እንዲህ ብሏልና {ከእርሱ ከተከላችሁት ታላላቆቹን (ሀጢአቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን) ሀጢአቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን።} [አንኒሳእ:31]