- የዉዱእና የትጥበት ውሃ ላይ ቆጣቢ መሆንና ውሃው ትንሽ ቢሆን እንኳ አለማባከን እንደሚገባ እንረዳለን።
- የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ ስለሆነ እንደአስፈላጊነቱ የዉዱእና የትጥበት ውሃን ማሳነስ እንደሚወደድ እንረዳለን።
- ከዉዱእና ትጥበት የሚፈለገው ሳይሰስቱና ሳያባክኑ አዳቡና ሱናውን ከመጠበቅ ጋር አሟልቶ መፈፀም ነው። ወቅቱን፣ የውሃውን ብዛትና ማነስ የመሳሰሉትን ግምት ውስጥ አስገብቶ ማድረግ ነው።
- ጀናባ የሚለው ስም የዘር ፈሳሽ ያፈሰሰ ወይም ግንኙነት የፈፀመ ሁሉ የሚገለፅበት ስም ነው። በዚህም የተሰየመው እስኪፀዳ ድረስ ግለሰቡ ከሶላትና ከአምልኮ ስለሚርቅ ነው።
- ቁና: የታወቀ መለኪያ ነው። የተፈለገውም ነቢያዊው ቁና ነው። የሚመዝነውም ጥሩ በሆነ የስንዴ ዘር (480) ግራም የሚመዝን ነው። በሊትር ደግሞ (3 ሊትር) የሚይዝ ነው።
- እፍኝ: አንዱ ሸሪዓዊ መስፈሪያ ነው። እርሱም መካከለኛ የሆነ ሰው መዳፍ እጁን ዘርግቶ በሁለት እጁ የሚዘግነውን ያህል ማለት ነው። አንድ እፍኝ በፉቀሃዎች ባጠቃላይ ስምምነት የአንድ ቁና ሩብ ነው። መጠኑም (750) ሚ·ሊ ይመዝናል።