- የሃይማኖቱ መሰረት በአላህ ጌትነት፣ ተመላኪነትና በስምና ባህሪያቶቹ ማመን ነው።
- ከማመን በኋላ ቀጥ የማለትን፣ በአምልኮ ላይ የመዘውተርና በዚህም ላይ የመፅናትን አንገብጋቢነት እንረዳለን።
- ኢማን ሥራዎች ተቀባይነት እንዲኖራቸው መስፈርት ነው።
- በአላህ ማመን ሲባል ማመን ግዴታ የሚሆንባቸውን እምነታዊ ጎዳዮችና መሰረቶችን፣ ይህንንም ተከትለው የሚመጡ የቀልብ ተግባራትን፣ በውስጥም ይሁን በውጪ ታዛዥነትንና እጅ መስጠትን ያጠቃልላል።
- "ኢስቲቃማ" (ቀጥ ማለት) ሲባል ግዴታዎችን በመስራትና ክልክሎችን በመተው ቀጥተንኛውን ጎዳና አጥብቆ መያዝ ማለት ነው።