ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሊት የተነሱ ጊዜ አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁ ነበር።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አብዝተው የሚፍቁና በመፋቅም ላይ የሚያዙ ነበሩ። አንዳንድ ወቅቶች ላይም አጠንክረው ሱናውን ይተገብሩ ነበር። ከነዛም ወቅቶች መካከል: ሌሊት በሚቆሙበት ወቅት መፋቅ ነው። ነቢዩ (የ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "በአማኞች ላይ ወይም በኡመቴ ላይ እንዳይከብዳቸ...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከኡመታቸው መካከል አማኞች ለሆኑት እንዳይከብድባቸው ባይሰጉላቸው ኖሮ ከሁሉም ሶላቶች ጋር መፋቂያን መጠቀም ግዴታ ያደርጉት እንደነበር ተናገሩ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ...
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ለአቅመ አዳምና የደረሰና አዕምሮው ጤነኛ በሆነ ሙስሊም ላይ ሁሉ በሳምንት ውስጥ ካሉት ሰባት ቀናት አንዱን ቀን የመታጠብ የጠበቀ ሀቅ እንዳለበት ተናገሩ። በዚህ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ና...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመልክተኞች ሱናዎችና ከኢስላማዊ መገለጫዎች አምስቱን አብራሩ፦ የመጀመሪያው፦ መገረዝ ነው። እሱም ከወንድ ልጅ ብልት ከክርክሩ ከፍ ብሎ ያለውን ጭማሪ ቆዳና ከሴት ልጅ ብልት ደ...
ከዐሊ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም...
ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መዚይ (ነጭ፣ ቀጭን፣ የሚዝለገለግ፣ ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት ወይም ከግንኙነት በፊት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) ብዙ ጊዜ ይወጣቸው እንደነበር ተናገሩ። መውጣቱን...

ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሊት የተነሱ ጊዜ አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁ ነበር።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "በአማኞች ላይ ወይም በኡመቴ ላይ እንዳይከብዳቸው ብዬ ነው እንጂ በሁሉም ሶላቶች ወቅት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት ።

ከዐሊ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (ስለብይኑ) መጠየቅ አፈርኩና ሚቅዳድ ቢን አስወድን እንዲጠይቃቸው አዘዝኩት፤ ጠየቃቸው። እርሳቸውም 'ብልቱን ይታጠብና ዉዱእ ያድርግ።' አሉ።" በቡኻሪ ዘገባ ደሞ "ዉዱእ አድርግ፤ ብልትህንም እጠብ።"

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር። ከዚያም በእጃቸው ፀጉራቸውን ይፈለፍላሉ። (የፀጉራቸው) ቆዳ በውሃ መራሱን እስከሚያስቡ ድረስም እየፈለፈሉ በጭንቅላታቸው ላይ ሶስት ጊዜ ውሃን ያፈሳሉ። ከዚያም ቀሪ ሰውነታቸውን ያጥባሉ።" ዓኢሻ እንዲህም ብላለች: "እኔና የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአንድ እቃ ሁለታችንም እየዘገንን እንታጠብ ነበር።"

ከዓማር ቢን ያሲር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለአንድ ጉዳይ ላኩኝና የዘር ፈሳሽ ወጣኝ። ውሃ አላገኘሁምና እንስሳ መሬት ላይ እንደምትንከባለለው ተንከባለልኩኝ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣሁና ይህን ድርጊቴ አወሳሁላቸው። እርሳቸውም 'በእጅህ እንዲህ ብታደርግ በቂህ ነበር።' አሉና ከዚያም በሁለት እጃቸው መሬቱን አንድ ጊዜ መቱ። ከዚያም በግራ እጃቸው ቀኝ እጃቸውን አበሱ። የላይኛውን የመዳፋቸው ክፍልንና ፊታቸውን አበሱ።"

ከሙጊራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "አንድ ጉዞ ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩና ኹፋቸውን (የቆዳ ካልሲያቸውን) ላወልቅ ዝቅ አልኩ፤ እሳቸውም: ' እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።' አሉኝና በነርሱ ላይ አበሱ።"

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው ፋጢማ ቢንት አቢ ሑበይሽ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ በማለት ጠየቀች: " 'እኔ የበሽታ ደም ይፈሰኛልና አልፀዳም። ሶላት ልተውን?' እርሳቸውም 'በፍፁም! ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አንዳችሁ ከሆዱ ውስጥ አንዳችን ነገር ያገኘ ጊዜ ከሆዱ አንዳች ነገር ወጥቷል ወይስ አልወጣም የሚለውን መለየት ካስቸገረው ድምፅ እስኪሰማ ወይም ሽታ እስኪያገኝ ድረስ (ሶላቱን አቋርጦ) ከመስጂድ አይውጣ።'"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።"»

ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' (ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለስ-ሶላህ' (ኑ ወደ ሶላት) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሀትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለል ፈላሕ' (ኑ ወደ ስኬት!) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሀትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜም 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።) ያለ ጊዜም 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' ካለ ጀነት ገባ።