- አላህ የሚወዳቸው፣ የሚቀበላቸውና ያዘዘባቸው የሆኑ የመልክተኞቹ ሱናዎች ወደ ምሉእነት፣ ንፅህናና ቁንጅና የሚጣሩ መሆናቸውን እንረዳለን።
- እነዚህን ነገሮች ተጠባብቆ መፈፀም የተደነገገ መሆኑንና ከነዚህ ጉዳዮች አለመዘናጋት እንደሚገባ እንረዳለን።
- እነዚህን ጉዳዮች በአግባቡ መፈፀም ዲናዊና አለማዊ ጥቅሞች አሉት። ከነሱም ውስጥ፦ አካልን ማስዋብ፣ ሰውነትን ማፅዳት፣ ለንፅህና ጥንቁቅ መሆን፣ ከሀዲያንን መቃረንና የአላህን ትእዛዝ መፈፀም ይገኝበታል።
- በሌላ ሐዲሥ ውስጥ ከነዚህ አምስት ተፈጥሯዊ ሱናዎች ውጪ ያሉ ተጨማሪ ሱናዎች፤ ለምሳሌ: ፂምን መልቀቅ (ማፋፋት)፣ ሲዋክና ሌሎችም ተጠቅሰዋል።