- ኢስላም ለንፅህናና ፅዳት ትኩረትና ቦታ መስጠቱን እንረዳለን።
- የጁሙዐ ቀን ለሶላቱ ብሎ መታጠብ አፅንኦት የተሰጠው ተወዳጅ ጉዳይ ነው።
- ገላን መታጠብ ሲባል ጭንቅላትም አብሮ ቢካተትም፤ ለብቻው የተጠቀሰው ትኩረት እንዲሰጠው ነው።
- ሰዎች በሚታወኩበት መልኩ መጥፎ ጠረን ያለበት ሰው የመታጠብ ግዴታ አለበት።
- ከመታጠቢያ ቀናቶች ሁሉ ተወዳጅነቱ የጠነከረ የሆነው ቀን ጁሙዐ ነው። ይህም ቀኑ ብልጫ ስላለው ነው።