- ሁለት ኹፎች ላይ ማበስ የተደነገገው ከትንሹ ሐደሥ (ዉዱእ አጥፍቶ) ዉዱእ በሚደረግበት ወቅት ነው። ለትልቁ ሐደሥ (ገላን ለሚያስታጥብ ጉዳይ) መታጠብ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ግን የግድ ሁለት እግሮችን መታጠብ ይኖርበታል።
- ኹፍ ላይ ማበስ የሚገኘው በውሃ በረጠበ እጅ ታችኛውን ሳይሆን ላይኛውን የኹፉ ክፍል አንድ ጊዜ በመዳበስ ነው።
- በሁለት ኹፎች ላይ ለማበስ ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶች አሉ። እነሱም: ኹፎቹን የሚለብሰው ሁለት እግሮቹን በውሃ ካጠበበት የተሟላ ዉዱእ በኋላ መሆን ይገባዋል፤ ኹፉ ንፁህና በትጥበት ወቅት ማጠብ ግዴታ የሆነውን የእግሩን ክፍል የሸፈነ መሆን ይገባዋል፤ የሚያብሰው በጀናባ (የዘር ፈሳሽ መጥቶት ወይም ግንኙነት በማድረጉ) ወይም ገላን የሚያስታጥቡ ነገሮች ሲያጋጥሙት ሳይሆን በትንሹ ሐደሥ (ውዱእ የሚያስደርጉ ምክንያቶች ሲያጋጥሙት) ብቻ መሆን ይገባዋል፤ የሚያብሰውም በሸሪዓ በተወሰነው ወቅት መሆን ይገባዋል። እሱም መንገደኛ ላልሆነ አንድ ቀን ከነምሽቱ ሲሆን ጉዞ ላይ ላለ ደግሞ ሶስት ቀን ከነሌሊቱ ነው።
- እንደካልሲና የመሳሰሉት ሁለት እግሮችን የሚሸፍኑ ሁሉ እንደ ሁለቱ ኹፎች ተመሳሳይ ፍርድ ስላላቸው በነርሱ ላይም ማበስ ይበቃል።
- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙጚራ ኹፋቸውን እንዳያወልቅ ሲከለክሉት ነፍሱ እንድትረጋጋና ብይኑን እንዲያውቅ ምክንያታቸውን መግለፃቸው የርሳቸው ስነምግባርና የማስተማር መንገዳቸው ማማሩን ያስረዳናል።