ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦ "ሙአዚኑን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት አዛን የሚያደርግን ሰው የሰማ ከ"ሐይየዐለተይን" ውጪ ከኋላው አስከትሎ (ሙአዚኑ) የሚለውን አምሳያ እንዲል ጠቆሙ። ከ"ሐይየዐለተይን" በኋላ ግን "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ...
ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: አዛን አድራጊውን የሰማ ጊዜ እንዲህ ያለ ሰው: "አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ" ማለትም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ከርሱ ውጪ የ...
ከጃቢር ቢን ዐብዲላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አዛን በሚሰማ ጊዜ ‹አ...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አዛን ባይን በሚሰማ ጊዜ አዛኑን ካጠናቀቀ በኋላ እንዲህ የሚል ሰውን ገለፁ። (የዚህ የተሟላ ጥሪ ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ!) የተሟላ ጥሪ የተባለው ወደ...
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአዛንና ኢቃም...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ ያለውን ደረጃና እርሱ ለተቀባይነት የተገባና የማይመለስ ስለሆነ በዚህ ወቅት አላህን እንድንማፀን ገለፁ።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ አንድ ማየት የተሳነው ሰውዬ መጣ። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ወደ መስጂድ የሚመራኝ መሪ የለኝም።' በማለት የአላ...
አንድ አይነ ስውር ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ዘንድ ለአምስቱ ሶላቶች እጄን ይዞ ወደ መስጂድ የሚወስደኝና የሚያግዘኝ የለም።" አለ። ፍላጎቱ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀማዓን በመተ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦ "ሙአዚኑን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ። እነሆ በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል። ከዚያም ለኔ ከአላህ ወሲላን ጠይቁልኝ። እርሷም ጀነት ውስጥ ያለች ደረጃ ናት። ከአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ አትገባም። እርሱም እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ወሲላን ለኔ የጠየቀልኝ ሰው ለርሱ ምልጃዬ ትፀናለታለች።"

ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ ይማራል።" (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ፤ በአላህ ጌትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።)

ከጃቢር ቢን ዐብዲላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አዛን በሚሰማ ጊዜ ‹አልላሁመ ረበ ሀዚሂ አድደዕወቲ አትታመቲ ወስሰላቲል ቃኢመህ አቲ ሙሐመደኒል ወሲለተ ወልፈዲለተ ወብዐሥሁ መቃመን መሕሙደኒለዚ ወዐድተህ› ያለ ሰው የትንሳኤ ቀን ምልጃዬ ትፀድቅለታለች።" ትርጉሙም "የዚህ የተሟላ ጥሪና የምትቆመው ሶላት ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ! ለሙሐመድ ወሲላና ፈዲላን ስጣቸው፤ ቃል የገባህላቸውን ምስጉን ስፍራም ስጣቸው።" ማለት ነው።

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።"»

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ አንድ ማየት የተሳነው ሰውዬ መጣ። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ወደ መስጂድ የሚመራኝ መሪ የለኝም።' በማለት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በቤቱ መስገድን እንዲያገሩለት ጠየቀ። ለርሱም አግራሩለት። ለመሄድ የዞረ ጊዜ ጠሩትና 'የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ፦ "'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?' ሶሐቦችም 'ከእድፉ አንዳችም አያስቀርም።' አሉ። እርሳቸውም 'ይህ የአምስቱ ሶላቶች ምሳሌ ነው። አላህ በሶላት ወንጀሎችን ያብሳል።' አሉ።"

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስራ ምን እንደሆነ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም 'ሶላትን በወቅቱ መስገድ።' አሉ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ቀጥሎ ለወላጆች መልካም መዋል ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ። እነዚህን ነገሩኝ። ጥያቄዬን ብጨምር እርሳቸውም ይጨምሩልኝ ነበር።"

ከዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ: 'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው እንጂ፤ ይህም እድሜልኩን ነው።'"

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ይሉ ነበር፡ "ከባባዶቹን ወንጀሎች ከተጠነቀቁ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።"

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጣዕረ ሞት ባጋጠማቸው ጊዜ አብዝተው ይመክሩት የነበሩት ምክር " ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ! ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ!" የሚል ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ይህን ምክር ከልባቸው ጉሮሯቸው ድረስ እስኪተናነቃቸው ደጋግመው ይሉት ነበር። ነገር ግን ምላሳቸው ልታወጣው ይሳናቸው ነበር።"

ዐምር ቢን ሹዐይብ ከአባቱና ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ብለዋል፦ "ከፍ ያለው አላህ እንዲህ አለ: 'ሶላትን በኔና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፈልኩት። ለባሪያዬም የጠየቀው አለው። ባሪያዬ {الْحَمْدُ لِلهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ} (ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው፤ የዓለማት ጌታ ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህ 'ባሪያዬ አመሰገነኝ!' ይላል። ባሪያው {الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ} (እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህ 'ባሪያዬ እኔን አወደሰ!' ይላል። ባሪያው {مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ} (የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህም 'ባሪያዬ አላቀኝ!' ይላል። - እንዲሁም 'ባርያዬ ጉዳዩን ወደ እኔ አስጠጋ።' - ይላል። ባሪያው {إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ} (አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን።) ያለ ጊዜ አላህም 'ይህ በኔና በባሪያዬ መካከል ያለ ቃል ኪዳን ነው። ለባሪያዬም የጠየቀውን አለው።' ይላል። ባሪያው {اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ، صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلا الضَّالِّينَ} (ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፤ የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ።) ) ያለ ጊዜ አላህም 'ይህ ለባሪያዬ ነው። ለባሪያዬም የጠየቀው አለው።' ይላል።"