- ይህን ዱዓ ከሙአዚን ኋላ የሚለውን ከደጋገሙ በኋላ ሲያጠናቅቅ ማለቱ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን። አዛን ያልሰማ ሰው ግን ይህን ዱዓ አይልም።
- ወሲላን፣ ፈዲላን፣ ምስጉን ስፍራንና በፍጡራን መካከል ፍርድ እንዲካሄድ ትልቁን ምልጃ ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መሰጠቱ የርሳቸውን ደረጃ ያሳየናል።
- "የትንሳኤ ቀን ምልጃዬ ትፀድቅለታለች።" ከሚለው ንግግራቸው መልክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደሚያማልዱ እናፀድቃለን።
- የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምልጃ ከኡመታቸው ትላልቅ ወንጀል ለሰሩት እሳት እንዳይገቡ እና እሳት ለገቡት ደግሞ እንዲወጡ ማማለድ ነው። ወይም ወደ ጀነት ያለሒሳብ እንዲገቡ ማማለድ እና ጀነት የገቡትም ደረጃቸው ከፍ እንዲል ማማለድ ነው።
- ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: «የተሟላች ጥሪ የተባለችው ከመጀመሪያው የአዛን ክፍል "ሙሐመደን ረሱሉሏህ" እስከሚለው ድረስ ያለው ነው። ሶላትን የሚያቋቁሙ በሚለው ውስጥ የቆመች የተባለችው ሶላት ደግሞ "ሐየዐለህ" ናት። ሶላት በማለት የተፈለገው ዱዓ፤ የቆመችው በማለት የተፈለገው ደግሞ ዘውታሪ ሊሆንም ያስመቻል። በአንድ ነገር የዘወተረ ጊዜ ቆመ እንደሚባለው ማለት ነው። በዚህም መሰረት "የቆመችው ሶላት" የሚለው የተሟላች ጥሪ ለሚለው መግለጫ ነው። ሶላት በማለት የተፈለገው አሁን አዛን እየተጠራላት ያለችው ሶላት ለማለት ተፈልጎ ሊሆንም ይችላል። ቃሉ በግልፅ የሚያስረዳውም ይህንኑ ነው።»
- ሙሀለብ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በሶላት ወቅቶች ዱዓ ማድረግ ላይ ያነሳሳል። በአዛን ወቅት ዱዓ ማድረግ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ ተስፋ የሚደረግበት ወቅት ነውና።"