- የሙአዚንን ጥሪ በመመለስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- ለሙአዚን ከመለስን በኋላ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላት የማውረድን ትሩፋት እንረዳለን።
- ሶላት ካወረድንባቸው በኋላ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወሲላን በመጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- የወሲላ ምንነትና ጉዳዩዋ ከፍ ያለ መሆኑ መገለፁ። ለአንድ ባሪያ እንጂ አትበጅምና (አትገባም)።
- በዚህች ከፍተኛ ደረጃ በመነጠላቸው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ደረጃ መገለፁ።
- ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአሏህ ወሲላን የጠየቀላቸው ሰው የርሳቸው ምልጃ ትፀድቅለታለች።
- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺ ደረጃ የርሳቸው ከመሆኗም ጋር ኡመታቸው ዱዓ እንዲያደርጉላቸው መፈለጋቸው ትህትናቸውን ይገልፃል።
- መልካም ስራ በአስር ማብዛቱ የአላህ ትሩፋትና እዝነት ስፋቱን ያስረዳናል።