ከእናትችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻ...
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሰጋጅ ነፍስ የሚጓጓውና ልቡ የተንጠለጠለበት ምግብ ቀርቦ መስገድን ከለከሉ። ልክ እንደዚሁ በቆሻሻው ግፊት ስለሚጠመድም ሁለቱ ቆሻሾች እያጨናነቁት (እነርሱም ሽን...
ከዑሥማን ቢን አቢል ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ እ...
ዑሥማን ቢን አቢልዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ መካከል ጋሬጣ ሆነ በ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹ከሚሰርቁ ሰዎች ሁሉ እጅግ መጥፎው ሶላቱን...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በስርቆት እጅግ በጣም መጥፎ ሰው ከሶላቱ የሚሰርቅ ሰው መሆኑን ገለፁ። ይህም ከዚህ ሌባ ተቃራኒ የሌላን ሰው ገንዘብ የወሰደ በዚህች አለም ሊጠቀምበትም ይችል ይሆናል። ይህ ሌባ ግን...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጭንቅላቱን ከኢማሙ በፊት ቀና የሚያደርግ ሰው አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት ሊያደርግበት ወይም የሰውነት ቅርፁን የአህያ ቅርፅ ሊያደርግበት እንደሚችል በመግለፅ ከባድ ዛቻን አስ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሰጋጅ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜና ሶስት ይሁን አራት ስንት እንደሰገደ ካላወቀ ምን ማድረግ እንዳለበት ገለፁ። ሶስተኛው ስለሆነ የተረጋገጠው አጠራጣሪውን የረከዓ ብዛት (አ...

ከእናትችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።"

ከዑሥማን ቢን አቢል ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ እንዲሁም በቂረአቴ መካከል አዘናጋኝና በኔ ላይ ያለባብስብኛል።" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!" አሉት። እርሱም "ይህንን ፈፀምኩ አላህም አስወገደልኝ።" አለ።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹ከሚሰርቁ ሰዎች ሁሉ እጅግ መጥፎው ሶላቱን የሚሰርቅ ነው።› እርሱም ‹እንዴት ሶላቱን ይሰርቃታል?› አላቸው። እርሳቸውም ‹ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን ባለማሟላት።› ብለው መለሱለት።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!"

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜ ሶስት ይሁን አራት ስንት እንደሰገደ ካላወቀ ጥርጣሬውን ይጣልና እርግጠኛ በሆነበት ላይ ይገንባ። ከዛም ከማሰላመቱ በፊት ሁለት ሱጁዶችን ይውረድ። አምስት ከሰገደ ሁለቱ ሱጁዶች ሶላቱን ጥንድ ያደርጉለታል። አራት ሞልቶ ከሰገደ ደግሞ ሱጁዶቹ ሰይጣንን ማዋረጃ ይሆኑለታል።"»

ከዋቢሰህ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሰውዬ ከሰልፍ ኋላ ብቻውን ሲሰግድ ተመለከቱትና ሶላቱን እንዲደግመው አዘዙት።"

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።»

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን ኣደም ተፈጠረ፣ በዚሁ ቀን ጀነት ገባ፣ በዚሁ ቀን ከርሷ ወጣ፣ ሰአቲቱም በጁመዓ ቀን ካልሆነ በቀር አትከሰትም።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ «የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሁለተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የከብት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሶስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ ቀንዳም ሙክት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በአራተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የዶሮ ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በአምስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የእንቁላል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። ኢማሙ ለኹጥባ የወጣ ጊዜ መላእክቶቹም ተግሳፁን ለመስማት ይገኛሉ።»

ከሠውባን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ (ምህረት ይጠይቁ) ነበር። እንዲህም ይሉ ነበር: 'አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም' (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) ወሊድ ለአውዛዒይ 'እንዴት ነው ኢስቲግፋር የሚደረገው? አልኩት' አለ። እሳቸውም 'አሰተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ' በማለት ነው ብለው መለሱልኝ።' አለ።"

ከአቡ ዙበይር እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ኢብኑ ዙበይር በሁሉም ሶላት ካሰላመተ በኃላ እንዲህ ይሉ ነበር። 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ፤ ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ ፤ ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወላነዕቡዱ ኢላ ኢያህ ለሁ አንኒዕመህ ወለሁልፈዽል ወለሁ አሥሠናኡል ሐሰን፤ ላኢላሃ ኢለሏሁ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲነ ወለው ከሪሃል ካፊሩን' አስከትለውም እንዲህ አሉ ' የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'"

የሙጚራ ቢን ሹዕባ ጸሐፊ ከሆነው ወራድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ሙጚራ ቢን ሹዕባ ወደ ሙዐዊያህ የሚጻፍን እንዲህ የሚል ደብዳቤ አጻፈኝ: 'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር ‹ላኢላሀ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁመ ላማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላ የንፈዑ ዘልጀዲ ሚንከልጀድ› ትርጉሙም 'ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛና ለርሱ አጋር የሌለው ነው። ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ማንም ከልካይ የለውም። ለከለከልከውም ማንም ሰጪ የለውም። የክብር ባለቤትም ክብሩ ካንተ (ቅጣት) አያድንም።'"