- የጁመዓ ቀን በመታጠብ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም ወደ ሶላት ከመሄድ በፊት ነው የሚፈፀመው።
- ወደ ጁመዓ ሶላት በቀኑ የመጀመሪያ ሰአት ማልዶ የመሄድን ትሩፋት እንረዳለን።
- ወደ መልካም ስራዎች በመቻኮል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- መላዕክቶች የጁመዓ ሶላትንና ኹጥባን ለማዳመጥ እንደሚገኙ እንረዳለን።
- መላዕክቶች በመስጂድ በሮች ላይ ሆነው ወደ ጁመዓ ሶላት የሚመጡ ሰዎችን አንድ በአንድ ይፅፋሉ።
- ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ብለዋል: "የጁመዓ ቀን የታጠበና ቀጥሎ ማልዶ የሄደ ሰው" የሚለው አነጋገር ለጁመዓ ተብሎ መታጠብ የሚወደደው መጀመሪያው ጎህ ሲወጣ ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ወደ ጁመዓ ሲሄድ መሆኑን ይጠቁማል።