- አንድ ተከታይ ከኢማሙ ጋር ያለው የመከተል ሁኔታ አራት ነው። ከአራቱ ሶስቱ የተከለከሉ ናቸው። እነርሱም: መቅደም፣ እኩል መፈፀምና ኋላ መቅረት ናቸው። ለተከታይ የተደነገገው ኢማሙን መከተል ነው።
- ተከታይ የሆነ ሰው ሶላት ውስጥ ኢማሙን መከተል ግዴታው እንደሆነ እንረዳለን።
- ከኢማሙ በፊት ራሱን ቀና የሚያደርግ ሰው ላይ የሰውነት ቅርፁ ወደ አህያ ቅርፅ እንደሚለወጥ የመጣው ዛቻ ሊሆን የሚችል ነገር ነው። ይህም ወደ ሌላ ፍጥረት ከመለወጥ የሚመደብ ነው።