- ሰጋጅ የሆነ ሰው ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜና እርሱ ዘንድ አንዱ ሚዛን ካልደፋ ጥርጣሬውን ይጥልና እርግጠኛ በሆነበት ነገር ላይ ይሰራል። ይሀውም አነስተኛ የሆነውን ነው (የሰገድኩት ሶስት ረከዓ ነው ወይስ አራት ብሎ ከተጠራጠረ ሶስት የሚለውን ይወስዳል)። ሶላቱን አሟልቶ ይሰግድና ከማሰላመቱ በፊት የመርሳት ሱጁድን ይወርዳል፤ ከዚያም ያሰላምታል።
- እነዚህ ሁለት ሱጁዶች ሶላትን መጠገኛ መንገድና ሰይጣንን ከፍላጎቱ የተዋረደ፣ የራቀና ባዶውን መመለሻ ናቸው።
- ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው ጥርጣሬ ሚዛን ያልደፋውን ጥርጣሬ ነው እንጂ ጥርጣሬው ሚዛን የሚደፋ ከሆነ ግን ሚዛን በሚደፋው ነው የሚሰራው።
- ሸሪዓዊን ትእዛዝ በመፈፀም ወስዋስን መዋጋትና መከላከል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።