- የህብረት ሶላት ለመስገድ በጊዜ መስጂድ በመግባትና ወደፊት ቀደም በማለት መነሳሳቱን እንረዳለን። ሶላቱ ለመበላሸት እንዳትጋለጥም ከሰልፍ ኋላ ለብቻው አለመስገድንም ያነሳሳል።
- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ሶላትን ከሰልፍ ኋላ ለብቻው ከጀመረ በኃላ ከሩኩዕ ከመነሳቱ በፊት ወደ ሰልፍ የገባ ሰው በአቢ በክራህ ሐዲሥ ውስጥ እንደመጣው የመድገም ግዴታ የለበትም። ያለበለዚያ ግን የዋቢሰህ ሐዲሥ ጥቅል ሀሳብ እንደሚያስረዳን የመድገም ግዴታ ይጠበቅበት ነበር።»