- ከሁሉም የሳምንቱ ቀናቶች የጁሙዓ ቀን በላጭ መሆኑን እንረዳለን።
- በጁሙዓ ቀን መልካም ስራዎችን በማብዛት ላይ፣ የአላህን እዝነት ለማግኘት በመዘጋጀትና መአቱን በመከላከል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሱት እነዚህ የጁመዓ ቀን መለዮዎች እንጂ የጁመዓን ቀን ደረጃ ለመጥቀስ ተብለው የተወሱ አይደሉም። የአደም ከጀነት መውጣትና የትንሳኤ ቀን መቆም ደረጃ ተደርገው አይቆጠሩም ያሉ ሲኖሩ፤ በሌላ በኩል ደሞ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት ሁሉም ደረጃዎች ናቸው። የአደም ከጀነት መውጣት ከመልክተኞች፣ ከነቢያቶችና ከደጋጎች የሆኑ ዘሮችን ለማግኘት ሰበብ ሲሆን የትንሳኤ መቆም ደግሞ የደጋጎች ምንዳ ለመፍጠኑና አላህ ለነርሱ ያዘጋጀላቸውን መከበሪያ ለማግኘት ሰበብ ስለሆነ ያሉም አሉ።
- በዚህ ዘገባ ያልተጠቀሱ በሌላ ዘገባ ግን የተጠቀሱ የጁመዓ ቀን ሌሎች መለዮዎችም አሉ። ከነሱም መካከል: በጁመዓ እለት አላህ የአደምን ተውበት ተቀበለ፣ በጁመዓ እለት ሞተ፣ በዚህች ቀን አንድ አማኝ ባሪያ እየሰገደ አላህን አንዳች ነገር እየጠየቀ ይህቺን ሰዓት አያገኝም አላህ የጠየቀውን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ የተባለላት አንዲት ሰዓት አለች።
- በዓመት ከሚገኙ ቀናቶች በላጩ ቀን የዐረፋ ቀን ነው። የእርድ ቀን ነው ያሉም አሉ። ከሳምንት ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓ ቀን ነው። በላጩ ምሽት ደግሞ የለይለተል ቀደር ምሽት ነው።