ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ አብዝተው ያደርጉት የነበረው ዱዓ 'አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠቅላይ የሆኑ ዱዓዎችን ማድረግ ያበዙ ነበር። ከነርሱም መካከል: "አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር" የሚለው ነበር።" (ትርጉሙም:...
ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸውን እንዲህ በማለት ጠየቁ : ልዕለ ኃያሉ ንጉሱ አላህ ዘንድ በላጩን፣ የላቀውን፣ የፋፋውን፣ የፀዳውንና የጠራውን ስራችሁን እንድነግራችሁ ትፈልጋላችሁን? ? ጀነ...
ከሙዓዝ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ : «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ጉዞ ላይ ነበርኩ። አንድ እለት እየተጓዝን ሳለ ወደ...
ሙዓዝ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ጉዞ ላይ ነበርኩ። አንድ እለት እየተጓዝን ሳለ ወደርሳቸው ቀረብ አልኩኝና እንዲህ አልኳቸው...
ከምእመናን እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው፦ "ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት...
ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መመሪያ መካከል ለመተኛት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ ልክ ዱዐ እንደሚያረግ ሰው መዳፋቸውን ሰብስበው ከፍ ያደርጉት ነበር። በሱም ላይ ከትንሽ ምራቅ ጋር በመቀላቀል ቀለል ያለ መንፋት በ...
ከሸዳድ ቢን አውስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲጝፋር) አለቃ 'አልላሁመ አንተ ረቢ ላ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምህረት የሚጠየቅበት የተለያዩ ቃላቶች እንዳሉና በላጩና ትልቁ አንድ ባሪያ እንዲህ ብሎ መጠየቁ እንደሆነ ተናገሩ: "አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ...

ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ አብዝተው ያደርጉት የነበረው ዱዓ 'አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር' የሚለውን ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው ዓለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።)

ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣ ለናንተ ወርቅና ብር ከመመፅወት የሚበልጥላችሁን ስራ፣ ጠላቶቻችሁን ተገናኝታችሁ አንገታቸውን ከምትመቱበት አንገታችሁን ከሚመቱበት ስራችሁም በላጩ የሆነውን ስራ አልነግራችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "አላህን ማውሳት ነው።" አሉ።»

ከሙዓዝ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ : «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ጉዞ ላይ ነበርኩ። አንድ እለት እየተጓዝን ሳለ ወደርሳቸው ቀረብኩኝና እንዲህ አልኳቸው: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝና ከእሳትም የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ?" እርሳቸውም " በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው። አላህን ልትገዛና በርሱ ላይ ምንንም ላታጋራ፤ ሶላትን ቀጥ ልታደርግ (በአግባቡ ልትሰግድ)፤ ዘካን ልትሰጥ፤ ረመዳንን ልትጾም፤ የአላህንም ቤት ሐጅ ልታደርግ ነው።" አሉና ቀጥለውም እንዲህ አሉ: "የመልካም ነገሮችን በር አልጠቁምህምን? ጾም ጋሻ ነው፤ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሁሉ ምፅዋትም ወንጀልን ታጠፋለች፤ የሰውዬው በሌሊቱ አጋማሽ የሚሰግደው ሶላት" አሉና ቀጥለው {ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ} ከሚለው {ይሰሩትም በነበሩት} እስከሚለው ድረስ [ሱረቱ ሰጅዳ: 16‐17] አነበቡ። ቀጥለውም "የነገሩ ሁሉ ራስ፣ ምሰሶውንና ሻኛውን ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልኳቸው። እርሳቸውም "የነገሮች ሁሉ ራስ (ዋና) እስልምና ነው፤ ምሰሶው ሶላት ነው፤ ሻኛው ጂሃድ ነው።" አሉ። ቀጥለውም "ይህን ሁሉ የሚቆጣጠረውን ነገር ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ ነቢይ ሆይ!" አልኳቸው። ምላሳቸውን ያዙና "በራስህ ላይ ይህቺን ቆጥባት!" አሉ። እኔም "የአላህ ነቢይ ሆይ! እኛ በምንናገረው እንያዛለንን?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ትጣህና ሙዓዝ ሆይ! ምላሳቸው ያጨደችው ካልሆነ በቀር ሰዎችን በፊታቸው ወይም በአፍጢማቸው እሳት ውስጥ የሚደፋቸው (ሌላ ነገር) አለ እንዴ?" አሉኝ።»

ከምእመናን እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው፦ "ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን ይቀሩበት ነበር። ከዚያም ከሰውነታቸው የቻሉትን በመዳፋቸው ያብሳሉ። (ሲያብሱም) ጭንቅላታቸውን፣ ፊታቸውንና ከሰውነታቸው የፊትለፊቱን በቅድሚያ ያብሳሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈፅሙታል።"

ከሸዳድ ቢን አውስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲጝፋር) አለቃ 'አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈጝፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየጝፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።' ማለትህ ነው።'" እንዲህም ብለዋል "በርሷ አምኖ ቀን ላይ ያላትና በዛው ቀን ከማምሸቱ በፊት የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው። በርሷ አምኖ ምሽት ላይ ያላትና ከማንጋቱ በፊት የሞተ ሰውም እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረሀኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።)

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: እርሳቸው ያነጉ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሰይና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ በአንተ አነጋን፣ በአንተም አመሸን፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" ያመሹ ጊዜ ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አምሰይና ወቢከ አስበሕና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" በሌላ ጊዜም እንዲህ ብለዋል "… ወኢለይከል መሲር" ትርጉሙም "… መመለሻም ወደ አንተ ነው።"

ከአባን ቢን ዑሥማን እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑሥማን ቢን ዐፋን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው: "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው: ‹ሶስት ጊዜ 'ቢስሚላሂለዚ ላየዱሩ መዐስሚሂ ሸይኡን ፊልአርዲ ወላፊስሰማእ ወሁወስ'ሰሚዑል ዐሊም' (ትርጉሙም: በዚያ ከስሙ ጋር በምድርም ይሁን በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳ በሆነው እንዲሁም ሰሚና አዋቂ በሆነው አላህ ስም።) ያለ ሰው እስኪነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ጊዜም ሶስት ጊዜ ያላት ሰው እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም።› አባን ቢን ዑሥማንን የግማሽ አካል ሽባነት አገኘውና ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም አተኩሮ ተመለከተው። አባንም ለርሱ እንዲህ አለው: እንደዚ አተኩረህ የምታየኝ ምን ሆነው ነህ? በአላህ እምላለሁ! በዑሥማን ላይ ምንም አልዋሸሁም! ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ምንም አልዋሸም። ነገር ግን ዛሬ የደረሰብኝ ነገር የደረሰው ተቆጥቼ ስለነበር ይህን ዚክር ማለት ረስቼ ስለነበር ነው።"»

ከዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "በዝናባማና በድቅድቅ ጨለማ ምሽት የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኛን እንዲያሰግዱን ፈልገን ወጣን። አገኘኋቸውና 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። ቀጥለውም 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። አሁንም 'በል!' አሉኝ። እኔም ምን ልበል? አልኳቸው። እርሳቸውም 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።"

ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ «በአንድ ምሽት የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከፍራሼ ላይ አጣኋቸው። በዳሰሳ ስፈልጋቸውም እጄ መስገጃቸው ላይ የተተከለችው የእግራቸው ውስጥ ላይ አረፈች። እርሳቸውም እንዲህ እያሉ ነበር " አላሁመ አዑዙ ቢሪዷከ ሚን ሰኸጢክ፣ ወቢሙዓፋቲከ ሚን ዑቁበቲክ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚንክ፣ ላኡሕሲ ሠናአን ዐለይክ አንተ ከማ አሥነይተ ዐላ ነፍሲክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ከቁጣህ በውዴታህ፣ ከቅጣትህ በይቅር ባይነትህ እጠበቃለሁ፤ ከአንተ በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ እራስህን ያወደስከውን ያህል ላወድስህ አልችልም።" ማለት ነው።

ከሰሙረህ ቢን ጁንዱብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። 'ሱብሓነላህ' (አላህ ሆይ! ጥራት ተገባህ) 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው።) 'ላኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) 'አሏሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) በማንኛቸውም ብትጀምር አይጎዳህም።"

ከአቡ አዩብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "አስር ጊዜ 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር' ያለ ሰው ከኢስማዒል ዘሮች የሆኑ አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ: ' 'ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ።'"