ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "መሃላ ሸቀጥን ተፈላጊ የሚያደርግ (የሚያዋድድ)፤ ትር...
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እውነተኛ ሆኖም ቢሆን በመሸጥና በመግዛት ወቅት ከመማልና መሃላን ከማብዛት አስጠነቀቁ። መሀላ ሸቀጡና እቃው እንዲፈለግ ምክንያት እንደሆነ ነገር ግን የትርፉና የስራውን በረከት የሚያጎ...
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመን...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀድሞ ቀመስን መቁረጥና አለመልቀቅን አዘዙ። እንደውም በደንብ መቁረጥ እንዳለበት ገለፁ። በተቃራኒው ሪዝን (የመንጋጭላን ፂም) መልቀቅና እንደበዛ መተውን አዘዙ።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከ...
ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ወደ ሌላ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቱን ወይም ሴት ልጅ ወደ ሌላ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቷን ከለከሉ። ሀፍረተ ገላ ማለት: ግልፅ የሆነ ጊዜ የሚያሳፍር የ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ...
ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መካከል ፀያፍ መናገር ወይም ፀያፍ ድርጊት አይገኝም ነበር። ትዝም አይላቸው። እሳቸው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የላቀ ስነምግባር ባለቤት ነበሩ። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉ ነበር...
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'...
መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው ቀኑን በመፆምና ሌሊቱን በመቆም የዘወተረ ሰውን ደረጃ እንደሚደርስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ። መልካም ስነምግባር ሲጠቀለል: መልካምን መለገስ፣ ንግግርን ማሳመር፣ ፊትን መፍታት፣ ሰውን ከመጉዳት...

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "መሃላ ሸቀጥን ተፈላጊ የሚያደርግ (የሚያዋድድ)፤ ትርፍን (በረከት) ደግሞ የሚያጠፋ ነው።"

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ!"

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት! ወንድ ልጅ ከሌላ ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አይጠቅለል! ሴት ልጅም ከሌላ ሴት ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አትጠቅለል!"

ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'"

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፡ 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ። በአብዛኛው ሰዎችን እሳት ስለሚያስገባቸው ነገርም ተጠየቁ። እሳቸውም "ምላስና ብልት ነው።" አሉ።

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ባጠቃላይ ይበልጥ ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ ሰው ነበሩ።"

ሰዕድ ቢን ሂሻም ቢን ዓሚር እናታችን ዓኢሻህ ዘንድ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- የገባ ወቅት እንዲህ አለ: "የሙእሚኖች እናት ሆይ! ስለአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ንገሪኝ! እሷም 'ቁርአን አትቀራምን?' አለችኝ። እኔም 'እንዴታ!' አልኩኝ። እሷም ' የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ስነምግባር ቁርአን ነበር።' አለችኝ።"

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።»

ከሸዳድ ቢን አውስ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: ሁለቱን ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ሸምድጃለሁ፦ "አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል። የገደላችሁ ጊዜ አገዳደላችሁን አሳምሩ፤ ያረዳችሁም ጊዜ አስተራረዳችሁን አሳምሩ። አንዳችሁ ቢላውን ይሞርድ እርዱንም ይገላግለው።"

ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ፦ የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው። (ፍትሃዊ የሚባሉትም) እነዚያ በፍርዳቸው፣ በቤተሰቦቻቸውና በተሾሙበት ጉዳዮች ላይ ፍትህን የሚያሰፍኑ ናቸው።"