- ቁርአናዊ ስነምግባር በመላበሳቸው ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አርአያ ማድረግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መሞገሱ። የሳቸው ስነምግባር ከወሕይ ምንጭ የተቀዳ ነውና።
- ቁርአን ለሁሉም የተከበሩ ስነምግባሮች ምንጭ መሆኑን እንረዳለን።
- ስነምግባር በኢስላም ሁሉንም የሃይማኖቱን ክፍሎች ያጠቃልላል፤ ይህም ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ ነው።