ከአቢ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ...
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጉዳትን በማንኛውም አይነት መገለጫው ይሁን ከነፍስ ላይም ይሁን ከሌሎች ላይ መከላከል ግዴታ እንደሆነ ገለፁ። ስለሆነም አንድም ሰው ራሱንም ይሁን በተመሳሳይ መልኩ ሌላንም ቢሆን ማወክ አይፈቀድለትም። እን...
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው።...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት አይነት ሰዎችን በምሳሌ ገለፁ። የመጀመሪያው አይነት: ወደ አላህ የሚጠቁም፣ ወደ አላህ ውዴታ የሚመራና በአምልኮ ላይ የሚያግዝ መልካም ጓደኛ ነው። የርሱም ምሳሌ ሽቶ እን...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: አንድ ሰውዬ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ: "ምከሩኝ!" እሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት። ጥያቄውን ደጋግሞ መላልሶ ጠየቃቸው እርሳቸውም "አት...
ከሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና አንዱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ የሚጠቅመውን ነገር እንዲጠቁሙት ፈለገ። እርሳቸውም እንዳይቆጣ አዘዙት። ይህም ማለት ወደቁጣ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን እንዲርቅ፣ የሚያስቆጣ ነገር በተ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።"
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትክክለኛ ሀይል አካላዊ ሀይል ወይም ጉልበተኞችን የሚጥል ሳይሆን ብርቱና ሀይለኛ የሚባለው ቁጣው በሚበረታ ወቅት ነፍሱን የታገለና ያሸነፋት መሆኑን ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ሰው ነፍሱን የመቆጣጠርና ሰይጣንን የ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አራት ነገሮች...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች አስጠነቀቁ። እነዚህ አራት ነገሮች አንድ ሙስሊም ላይ የተሰባሰቡ ጊዜ በነዚህ ነገሮች ሰበብ ከመናፍቃን ጋር እጅግ በጣም ይመሳሰላል። ይህ ግን...

ከአቢ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።"

ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው። ሽቶ ተሸካሚ ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይ ከርሱ መልካም መአዛን ታገኛለህ። ወናፍ ነፊ ደሞ ወይ ልብስህን ያቃጥላል ወይም ከርሱ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: አንድ ሰውዬ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ: "ምከሩኝ!" እሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት። ጥያቄውን ደጋግሞ መላልሶ ጠየቃቸው እርሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።"

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ጥርት ያለ ሙናፊቅ ይሆናል። ከነርሱ መካከል ከፊሉ ያለበት ሰው እስኪተወው ድረስ ከፊል ንፍቅና ይኖርበታል። ሲያወራ ይዋሻል፣ ቃልኪዳን ይዞ ያፈርሳል፣ ቀጠሮ ይዞ ያፈርሳል፣ ሲሟገት (ድንበር ያልፋል) በጥመት ላይ ነው።"»

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።"»

ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሰውዬ ወንድሙን በአይነአፋርነቱ ሲወቅሰው ሰሙና 'አይነአፋርነት ከኢማን ነው።' አሉት።

ከሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።"

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "መልካም ነገሮች ሁሉ ምፅዋት ናቸው።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሁሉም የሰው ልጅ መገጣጠሚያ አጥንቶች ምፅዋት አለባቸው። ፀሀይ በምትወጣበት ቀናት ሁሉ፤ በሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅ ምፅዋት ነው። ሰውዬውን መጓጓዣው ላይ እንዲወጣ ማገዝ ፣ እርሷ ላይ ማሸከም ወይም እቃውን እርሷ ላይ መጫን ምፅዋት ነው። መልካም ንግግር ምፅዋት ነው። ወደ ሶላት የሚራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ነው። ከመንገድ ላይ ቆሻሻን ማስወገድ ምፅዋት ነው።"»

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»

ከአቡ በርዛህ አልአስለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፦ "የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'"