ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መን...
ባሏ ለሞተባትና የሚያስፈልጋትን ጉዳይ የሚያሟላላት አንድም ሰው ለሌላት ሴት እና ተረጂ ለሆነ ሚስኪን ጥቅማቸውን በሟሟላት የቆመ እንዲሁም አላህ ዘንድ ምንዳን በማሰብ ለነርሱ ወጪ የሚያደርግ ሰው በምንዳ ደረጃ ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን...
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ እና መመለሻውም በስራው የሚመነዳበትም በሆነው መጨረሻው ቀን ያመነ ባሪያ ኢማኑ እነዚህን ጉዳዮችን በመፈፀም ላይ እንደሚያነሳሳው ገለፁ: የመጀመሪያው: መልካም መናገር ነው። በዚህ ውስጥ ሱብሓነላ...
ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉኝ: "ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።"
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካምን ከመፈፀም እንዳናሳንስ አነሳሱን። ከነዚህ መካከልም ከሙስሊም ጋር በሚገናኝ ወቅት በፈገግታ ፊትን መፍታት ይጠቀሳል። አንድ ሙስሊም ይህን በመፈፀሙ ምክንያት ሙስሊም ወንድሙን ማዝ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እ...
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እውነተኝነትን አዘዙ። እውነተኝነትን አጥብቆ መያዝ ለዘውታሪ መልካም ስራና በመልካም ስራ ላይም እንዲዘወትር የሚያደርገው በመሆኑ ሰውዬውን ወደ ጀነት እንደሚያደርሰው ተናገሩ። ሰውዬው...
ከጀሪር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።"
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሰዎች የማይራራ ሰውን የላቀውና የተከበረው አላህም እንደማይራራለት ገለፁ። ሰው ለፍጡር ማዘኑ የአላህን ርህራሄ ማግኛ ከሆኑ ትላልቅ ሰበቦች መካከል ነው።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ሰው አምሳያ ወይም ልክ ሌሊት እየሰገደ ቀኑን እንደሚፆም አምሳያ ነው›"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር!"

ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉኝ: "ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።"

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ እውነተኛ ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ እውነት ከመናገርና እውነትን ከመምረጥ አይወገድም። አደራችሁን ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል። ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ ከመዋሸትና ለውሸት ከመጣር አይወገድ።"

ከጀሪር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።"

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው፤ ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።"

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ "አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም። እስክትዋደዱ ድረስም አታምኑም። የፈፀማችሁት ጊዜ የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ልጠቁማችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ።'"

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:- "አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ" አሉ። እርሳቸውም "በአስቸጋሪ ወቅት ዉዱእን አዳርሶ ማድረግ፣ ወደ መስጂድ እርምጃ ማብዛት፣ አንድ ሰላት ካለቀ በኋላ ሌላኛው ሶላት መጠበቅ፤ ይሀው ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ) ናቸው።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው። በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ! በአላህም ታገዝ! አትስነፍ! አንዳች ነገር ሲያገኝህም ‹እንዲህ አድርጌ በነበር እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር።› አትበል። ይልቁንም ‹ይህ የአላህ ውሳኔ ነው። የሻውንም ፈፀመ።› በል። (እንዲህ ቢሆን ኖሮ) ማለት የሰይጣን ስራ ትከፍታለችና።'"