- እውነተኝነት በጥረትና በትግል የሚገኝ የተከበረ ባህሪ ነው። ሰውዬው እውነት የርሱ ባህሪና ተፈጥሮው እስኪሆን ድረስ እውነት ከመናገርና ለእውነትም ከመጣር አይወገድም።
- ውሸት ሰውዬው ባህሪውና መገለጫው እስኪሆንና ቀጥሎም አላህ ዘንድ ከውሸታሞች እስኪፃፍ ድረስ በመላመድ ብዛትና በንግግሩና በተግባሩ የሚያመጣው የተወገዘ ስነምግባር ነው።
- እውነት የሚለው ቃል በምላስ ለሚነገር እውነት ስያሜው ይሰጣል፤ ይህም የውሸት ተቃራኒ ነው። በኒያ ለሚኖር እውነትም ስያሜው ይሰጣል፤ ይህም ስራን ለአላህ ማጥራት (ኢኽላስ) ተብሎ ይጠራል። በነየተው መልካም ነገር ላይ ላለው እውነተኛ ቁርጠኝነትም ስያሜው ይሰጣል። በተግባር ለሚኖር እውነተኝነትም የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም ቢያንስ ውስጡና ውጪው እኩል መሆን አለባቸው። ስያሜው በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ እውነተኛነትን ለመላበስም ይሰጣል። ለምሳሌ አላህን በመፍራት፣ አላህን በመከጀልና በሌሎችም ሁኔታዎች እውነተኛ መሆንን ሁሉ ያጠቃልላል። በዚህ መልኩ እውነትን የተላበሰ እጅግ እውነተኛ (ሲዲቅ) ይባላል። በተወሰኑት ብቻ እውነተኛ ከሆነ ግን እውነተኛ ብቻ ነው የሚባለው።