- መስጂድ ውስጥ የህብረት ሶላትን የመጠባበቅ አንገብጋቢነቱን፤ ለሶላት ትኩረት መስጠትና ከሶላት በሌላ ነገር መጠመድ እንደሌለብንም እንረዳለን።
- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስራው የሚያስገኘውን ትልቅ ምንዳ በጥያቄያዊ መንገድ አስቀድመው ባልደረቦቻቸውን በማጓጓታቸው የትምህርት አቀራረባቸውን ማማር እንረዳለን። ይህም አንዱ የማስተማሪያ መንገድ ነው።
- አንድን ጉዳይ በጥያቄና መልስ መንገድ ማቅረብ ብይኑን መጀመሪያ በመደበቅና ቀጥሎ በማብራራት ንግግሩ ነፍስ ውስጥ እንዲቀር የማድረግ ጥቅም አለው።
- ነወዊ አላህ ይዘንላቸውና «ይህ ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ)» ማለት ተፈላጊው ዘብ መጠበቅ ይህ ነው ማለት ነው። ሪባጥ የሚለው ቃል መሰረት በአንድ ነገር ላይ መታጠር ማለት ሲሆን በነዚህ ስራዎች አላህን በመገዛት ላይ ነፍሱን ስለሚያጥር ነው። "ጂሃድ ማለት ነፍስን መታገል ነው።" እንደሚባለው በላጩ ሪባጥ ይህ ነውም ተብሏል። በሌላ አባባል ደሞ ቀላሉና የሚመቸው ሪባጥ ነው ማለት ተፈልጎበት ሊሆንም ያስመቻል። ማለትም ከሪባጥ አይነቶች አንዱ ነው እንደማለት ነው።
- (አል) የምትለዋ ገላጭ ገብታ "አር‐ሪባጥ" የምትለዋ ቃል መደጋገሟ የነዚህ ስራዎችን ትልቅነት ያስረዳናል።