- ሶሐቦች በዱንያም ሆነ በመጨረሻው ዓለም የሚጠቅመምን ጉዳይ ለማወቅ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።
- ሰላምታ ማቅረብና ምግብ ማብላት ሰዎች በሁሉም ወቅት የሚፈልጉት ስለሆነና በላጭ ስራ ከመሆኑ አንፃርበ ኢስላም ውስጥ ትልቅ ደረጃ ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል እንደሆኑ እንረዳለን።
- በነዚህ ሁለት ጉዳዮች ንግግራዊም ተግባራዊም በጎነት ይሰበሰባሉ። ይህም የተሟላው በጎነት ነው።
- እነዚህ ጉዳዮች ሙስሊሞች በመካከላቸው ሊኖራቸው ከሚገባው መስተጋብር ጋር የተያያዘ ሲሆን ሌላ ቦታ ደግሞ አንድ ባሪያ ከጌታው ጋር ሊኖረው ስለሚገባ መስተጋብር የሚገልፁ ጉዳዮች አሉ።
- በሰላምታ መጀመር በሙስሊሞች መካከል ብቻ የተገደበ ሲሆን ካፊር በሰላምታ አይጀመርም።