- በመተጋገዝ፣ ሀላፊነት በመወጣትና የደካሞችን አስፈላጊ ጉዳዮች በማሟላት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- አምልኮ ሲባል ሁሉንም መልካም ስራ ይሰበስባል። ከአምልኮዎች መካከልም ባሏ ለሞተባት ሴትና ለሚስኪን ጥቅም መልፋት አንዱ ነው።
- ኢብኑ ሁበይራ እንዲህ ብሏል: "ከዚህ ሐዲሥ የተፈለገው ከፍ ያለው አላህ የታጋይ (የሙጃሂድ)ና እየፆመ ሌሊት የሚቆምን ሰው ምንዳ በአንድ ጊዜ ይሰበስብለታል ማለት ነው። ይህም ባሏ ለሞተባት ሴት የባሏን ቦታ ተክቶ ስለተወጣ … ራሱን ችሎ መቆም ለተሳነው ሚስኪንም የተረፈውን ቀለብ ወጪ አድርጎ በአቅሙ ስለመፀወተ የሰጠው ጥቅም ፆም፣ የሌሊት ሶላትና ጂሀድን የሚመጥን ሆነ።"