ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'አላህ ዘንድ እጅግ ትልቁ ወንጀል ምንድነው?' ብዬ ጠየቅኩ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ እጅግ ትልቁ ወንጀል ተጠየቁ: እጅግ ትልቁ ወንጀል ትልቁ ሺርክ ነው። እርሱም ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ ምሳሌ ወይም ቢጤን ማድረግክ ነው።...
አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦ የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌ...
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ማለቱን እየነገሩን ነው፡- አጋርን ከመፈለግ ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃው አሏህ ነው። እርሱም ከምንም የተብቃቃ ራሱን የቻለ ነው። አንድ ሰው መልካም...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን እምቢ ይላል?" አሉ።...
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀነት ከመግባት ራሱን ያቀበ ሰው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ህዝባቸው ጀነት እንደሚገቡ ተናገሩ። ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ራሱን ከጀነት ያቅባል?" አሉ።...
ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡ "ክርስቲያኖች የመርየም ልጅን ሲያሞግሱ ወሰን እንዳለፉት እኔን ስታሞግሱ ወሰን አትለፉ። እ...
ክርስቲያኖች ዒሳ ዓለይሂ ሰላምን በተመለከተ ወሰን እንዳለፉት ሁሉ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ህዝባቸው እሳቸውን በማሞገስ በኩል፣ በአላህ ባህሪያትና ልዩ ድርጊቶቹ እሳቸውን በመግለፅ፣ የሩቅ እውቀትን እንደሚያውቁ...
ከአነስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'"
አንድ ሙስሊም ለአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያለው ውዴታ ለእናቱ ፣ ለአባቱ ፣ ለወንድ ልጁ፣ ለሴት ልጁና ለሰዎችም ባጠቃላይ ካለው ውዴታ እስኪያስቀድም ድረስ ኢማኑ ምሉዕ አይሆንም በማለት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለ...

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'አላህ ዘንድ እጅግ ትልቁ ወንጀል ምንድነው?' ብዬ ጠየቅኩ። እርሳቸውም 'አላህ ፈጥሮህ ሳለ ለርሱ ቢጤን ማድረግክ ነው።' አሉ። እኔም 'ይህማ ትልቅ ነው።' አልኩኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ልጅህን ከአንተ ጋር መብላቱን ፈርተህ መግደልክ ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በጎረቤትህ ሚስት ላይ ዝሙት መስራትህ ነው።' አሉኝ።"

አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦ የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን እምቢ ይላል?" አሉ። እሳቸውም "እኔን የታዘዘኝ ጀነት ገባ ፤ እኔን ያመፀኝ ደግሞ በርግጥም እምቢ ብሏል።" በማለት መለሱ።"

ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡ "ክርስቲያኖች የመርየም ልጅን ሲያሞግሱ ወሰን እንዳለፉት እኔን ስታሞግሱ ወሰን አትለፉ። እኔ የአሏህ ባሪያ ብቻ ነኝ። ስለዚህም የአላህ ባሪያና መልክተኛው በሉኝ።'"

ከአነስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ((የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በተውኳችሁ ላይ ተዉኝ። ከናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦች የጠፉት በመጠየቃቸውና ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸው ነው። ከአንዳች ነገር የከለከልኳችሁ ጊዜ ራቁት፤ በአንድ ትእዛዝ ያዘዝኳችሁ ጊዜ ደሞ የቻላችሁትን ያህል ከርሱ ፈፅሙ!"

ከዐብደሏህ ቢን ዐምር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አንዲትም አንቀጽ ቢሆን ከኔ አስተላልፉ። ከቤተ እስራኤላውያንም አውሩ ችግር የለውም። ሆን ብሎ በኔ ላይ የዋሸ መቀመጫውን ከእሳት ያመቻች።"

አልሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፡- “የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡- "አዋጅ! ከእኔ የሆነ ሐዲሥ ወደ አንዱ በአልጋው ላይ እንደተደገፈ ይደርሰውና፡ "በእኛና በእናንተ መካከል (የሚዳኘን) የአላህ መጽሐፍ ነው። በውስጡ የተፈቀደ ሆኖ ያገኘነውን (ብቻ) እንደ ሐላል እንቆጥረዋለን በውስጡም ሐራም ሆኖ ያገኘነውን (ብቻ) እንደ ሐራም እንቆጥረዋለን።" የሚልበት ወቅት ቅርብ ነው። በእርግጥ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሐራም (እርም) ያደረጉት ማንኛውም ነገር አላህ ሐራም እንዳደረገው ነው።'”

ከእናትችን ዓኢሻና ዐብደላህ ቢን ዓባስ - (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የሞት መልዐክ በአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ የወረደ ጊዜ ፊታቸው ላይ ጨርቃቸውን ጣል ማድረግ ጀመሩ ፤ ሲያፍናቸው ደግሞ ይገልጧት ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ 'በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።' አሉ፤ ከሰሩት ስራ እያስጠነቀቁ። '"

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፏል፡ "አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት አታድርግብኝ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው በያዙ ህዝቦች ላይ የአሏህ እርግማን ሰፈነባቸው።"

አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል: የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።"

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦ ኡሙ ሰላማ ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሀበሻ ምድር ማሪያህ በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላየቻቸው ምስሎች ነገረቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡- "እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡ፤ በውስጡም (ምስሉን) ስእላ ስእል የሚቀርፁ ናቸው። እነዚህ ህዝቦች አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ (መጥፎ) ፍጡራን ናቸው።"