ዋና ገፅ
እኛ ማን ነን
am
English
العربية
español
português
Français
Русский
اردو
azərbaycanca
Ўзбек
Deutsch
Shqip
فلبيني مرناو
براهوئي
български
বাংলা
ဗမာ
bosanski
polski
தமிழ்
ไทย
татар теле
română
isiZulu
سنڌي
සිංහල
Kiswahili
svenska
нохчийн мотт
Soomaali
тоҷикӣ
غجري
Pulaar
Pulaar
Tiếng Việt
قمري
कश्मीरी
한국어
македонски
bahasa Melayu
മലയാളം
magyar
हिन्दी
Hausa
Èdè Yorùbá
ελληνικά
қазақ тілі
فارسی
Türkçe
עברית
中文
Bahasa Indonesia
Wikang Tagalog
dansk
پښتو
Tamazight
አማርኛ
أنكو
ئۇيغۇرچە
Luganda
తెలుగు
日本語
ትግርኛ
غموقي
Кыргызча
नेपाली
Kurdî
italiano
Nederlands
čeština
українська
eesti
suomi
Адыгэбзэ
Norwegian
latviešu
slovenščina
монгол
íslenska
ქართული
tamashaq
ދިވެހި
Հայերէն
slovenčina
Afrikaans
Türkmençe
башҡорт теле
afaan oromoo
ភាសាខ្មែរ
ಕನ್ನಡ
Bassa
Lingala
lietuvių
bamanankan
Soninke
Malagasy
Mandinka
Sängö
Wollof
Cham
Qhichwa simi
Српски
Afaraf
hrvatski
Kinyarwanda
aymar aru
Jóola
Bi zimanê Kurdî
Akan
ଓଡ଼ିଆ
Chichewa
авар мацӀ
Igbo
isiXhosa
मराठी
Fɔ̀ngbè
ગુજરાતી
Mɛnde
ГӀалгӀай
Mõõré
অসমীয়া
Maguindanao
Dagbani
Yao
Ikirundi
Bisaya
Ruáingga
فارسی دری
Sesotho
ਪੰਜਾਬੀ
créole
ພາສາລາວ
ዋና ገፅ
እኛ ማን ነን
Contact Us
ጁንዱብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመሞታቸው አምስት (ሌሊቶች) በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡- ' እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያ...
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በአላህ ዘንድ ያላቸው ደረጃ አሳወቁ፤ ልክ እንደ ኢብራሂም ዐለይሂ ሰላም እሳቸውም ላእላይ እርከን የደረሰ ውዴታ መጎናፀፋቸውንም ተናገሩ። ከአሏህ ውጭ ፍፁም ወዳጅ ሊኖራቸው እንደማይችል...
ከአቢል ሀያጅ አልአሰዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ለኔ እንዲህ አለኝ: 'የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው...
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሓቦቻቸውን "ምስልን" (እሱም አካል ይኑረውም አይኑረው የነፍስ ያለው ነገር ምስል ነው።) ያስወገዱት ወይም ያወደሙት ቢሆን እንጂ እንዳይተዉት ይልኩ ነበር። ከፍ ያለ ቀብርንም ከምድር ጋር እኩል ያደረጉ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከገድ እምነት አስጠነቀቁ። እርሱም: በሚሰማም ይሁን በሚታይ ነገር፤ በበራሪም ሆነ በእንስሳም ሆነ በህመምተኞች (አካል ጉዳተኞች)፤ በቁጥሮችም ሆነ በቀናት ወይም ከነዚህ ውጪ ባሉ ማ...
ከዒምራን ቢን ሑሰይን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'የገድ ተግባርን የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት፣ ወይም የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ፣...
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በኡመታቸው ውስጥ አንዳንድ ተግባራት የፈፀሙ ሰዎችን "ከኛ አይደሉም!" በማለት ዛቱ። ከተግባራቱም፦ የመጀመሪያው: "ገድ ተግባር የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት" የዚህ አመለካከት መሰረት:- ጉዞ ወይም ን...
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በራሱ የሚተላለፍ ተላላፊ በሽታ የለም፣ ገድም የለም ተስፈኝነት (በጎ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሽታ ከአንዱ ወደ ሌላው ያለ አላህ ውሳኔ በራሱ ይተላለፋል የሚለው የድንቁርና ዘመን ሰዎች ያምኑት የነበረው እምነት የተሳሳተ ከንቱ እምነት መሆኑን ተናገሩ። የገድ እምነትም ከንቱ...
እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ
ጁንዱብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመሞታቸው አምስት (ሌሊቶች) በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡- ' እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ አድርጎ እንደያዘው ሁሉ እኔንም ፍፁም ወዳጅ አድርጎ ይዞኛልና። ከኡመቴ ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዝ ብሆን ኖሮ አቡበከርን ነበር ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዘው። አዋጅ! እነዚያ ከናንተ በፊት የነበሩት የነብያቶቻቸውንና የፃድቃኖቻቸውን መቃብር መስገጃ ስፍራ አድርገው ይይዙ ነበር። አዋጅ! መቃብርን መስገጃ ስፍራ አድርጋችሁ አትያዙ! እኔ እየከለከልኳችሁ ነው።'"
Hadeeth details
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው፤ ማንኛውም ከፍ ያለ ቀብርንም ያስተካከልከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው።'...
ከአቢል ሀያጅ አልአሰዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ለኔ እንዲህ አለኝ: 'የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው፤ ማንኛውም ከፍ ያለ ቀብርንም ያስተካከልከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው።'"
Hadeeth details
'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። (አሉ ሶስት ጊዜ)' ከኛ መካከል በልቡ የገድ እምነት የሚመጣበት እንጂ አንድም የለም። ነገር ግን አላህ በርሱ ላይ በመመካታችን ምክንያት ያስወግደዋል።...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። (አሉ ሶስት ጊዜ)' ከኛ መካከል በልቡ የገድ እምነት የሚመጣበት እንጂ አንድም የለም። ነገር ግን አላህ በርሱ ላይ በመመካታችን ምክንያት ያስወግደዋል።"
Hadeeth details
'የገድ ተግባርን የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት፣ ወይም የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ፣ ወይም የደገመ ወይም ያስደገመ፣
ከዒምራን ቢን ሑሰይን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'የገድ ተግባርን የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት፣ ወይም የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ፣ ወይም የደገመ ወይም ያስደገመ፣ ትብታብንም የተበተበ ከኛ አይደለም። ጠንቋይ ዘንድ የሄደና የሚናገረውን ነገር አምኖ የተቀበለ በሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ በወረደው ነገር በእርግጥ ክዷል።'"
Hadeeth details
በራሱ የሚተላለፍ ተላላፊ በሽታ የለም፣ ገድም የለም ተስፈኝነት (በጎ ምኞት) ግን ያስደስተኛል።" "አልፈእል (በጎ ምኞት) ምንድነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "መልካም ንግግር ነው።" አሉ።...
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በራሱ የሚተላለፍ ተላላፊ በሽታ የለም፣ ገድም የለም ተስፈኝነት (በጎ ምኞት) ግን ያስደስተኛል።" "አልፈእል (በጎ ምኞት) ምንድነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "መልካም ንግግር ነው።" አሉ።
Hadeeth details
ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ...
ዘይድ ቢን ኻሊድ አልጁሀኒይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሑደይቢያ ምሽት የዘነበን ዝናብ አስከትለው የንጋትን ሰላት አሰገዱን። ሰላቱን ያጠናቀቁ ጊዜም ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ "ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ። በአላህ ችሮታና እዝነት ምክንያት ዘነበልን ያለ በኔ ያመነ በከዋክብት የካደ ነው። በእንዲህ እንዲህ የኮኮብ እንቅስቃሴ ምክንያት ዘነበልን ያለ ደግሞ በኔ የካደና በከዋክብት ያመነ ነው።"
Hadeeth details
'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።
ከዑቅባህ ቢን ዓሚር አልጁሀኒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው፦ "ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተወሰኑ ሰዎች መጡ። ከዘጠኙ ጋር ቃልኪዳን ተጋቡና ከአንዱ ጋር ቃልኪዳን ከመጋባት ተቆጠቡ። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከዘጠኙ ጋር ቃልኪዳን ተጋብተው ይህንን ለምን ተዉ?' አሉ። እርሳቸውም 'እርሱ ላይ ሒርዝ ስላለ ነው።' አሉ። (ይህንን ሲሰማ) እጁን አስገባና ቆረጠው። እርሳቸውም ቃልኪዳን ተጋቡትና 'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።"
Hadeeth details
ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።"
Hadeeth details
ሩቅ አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደና ስለአንዳች ነገር የጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላቱ ተቀባይነት አይኖራትም።
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆኑት መካከል ከአንዷ እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ሩቅ አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደና ስለአንዳች ነገር የጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላቱ ተቀባይነት አይኖራትም።"
Hadeeth details
'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'
ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ሰሙ፡ "በካዕባ ይሁንብኝ በፍፁም!" ኢብኑ ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንዲሁ አሉ፡ "ከአሏህ ውጭ ባለ አካል አይማልም! ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁና 'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'"
Hadeeth details
(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።
ከቡረይዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"
Hadeeth details
እኔ ወላሂ አላህ ከሻ በአንድ ጉዳይ ከማልኩ በኋላ ተቃራኒው የተሻለ ሆኖ ከታየኝ የተሻለውን ፈፅሜ ለመሀላዬ ማካካሻ አደርጋለሁ እንጂ ከዚህ ውጪ ሌላ አላደርግም።" አሉን።...
ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ከተወሰኑ የአሽዐር ተወላጆች ጋር በመሆን ለጂሀድ መጓጓዣ እንዲሰጡን ለመጠየቅ መጣሁ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "በአላህ እምላለሁ! መጓጓዣ አልሰጣችሁም። እኔ ዘንድ የምሰጣችሁ መጓጓዣ የለኝም።" ከዚያም አላህ የሻው ወቅት ያህል ቆየን። ግመል መጣላቸውና ለኛም ሶስት ግመል እንዲሰጠን አዘዙ። ግመሉን ይዘን ጉዞ የወጣን ጊዜ አንዳችን ለአንዳችን "አላህ በዚህ ግመል አይባርክልንና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ የጂሀድ መጓጓዣ ግመል ፈልገን መጣን። እርሳቸውም መጓጓዣ እንደማይሰጡን ማሉና ቀጥሎ ሰጡን! (ለመሀላቸው ብለን መቀበል አልነበረብንም።)" ተባባልን።» አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት ይህንን አወሳንላቸው። እርሳቸውም "እኔ አይደለሁም መጓጓዣ የሰጠዋችሁ አላህ ነው የሰጣችሁ። እኔ ወላሂ አላህ ከሻ በአንድ ጉዳይ ከማልኩ በኋላ ተቃራኒው የተሻለ ሆኖ ከታየኝ የተሻለውን ፈፅሜ ለመሀላዬ ማካካሻ አደርጋለሁ እንጂ ከዚህ ውጪ ሌላ አላደርግም።" አሉን።»
Hadeeth details
‹
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
...
30
31
›
Share
Use the QR code to easily share the message of Islam with others
Copy Link
copied!
ተገናኘን
×
ስም
ኢሜይል
የጽሑፉ መልዕክት
ተገናኘን
×
መልክት በመላኪህ እናመሰግናለን ...አላህ ካለ እናየዋለን
Share