- ለወደፊት ለሚከሰት ነገር ቢሆንም እንኳ ንግግርን አፅንዖት ለመስጠት ሳያስምሉንም መማል እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
- ከመሀላ በኋላ "ኢን ሻኣ አላህ" -በአላህ ፈቃድ- በሚል ቃል መሀላችንን የአላህ ፈቃድ ላይ ማንጠልጠል እንደሚፈቀድ፤ አላህ ከሻ የሚለውን ቃል ከመሀላው ጋር ነይቶ መሀላውን አስከትሎ የተናገረው መሀላውን ባፈረሰ ሰው ላይ ማካካሻ ግዴታ አይሆንም።
- ከተማለበት ነገር ይልቅ ተቃራኒው የተሻለ ሆኖ ያገኘው ሰው መሀላውን ተቃርኖ ለመሀላው ማካካሻ በማውጣት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።