- ተውሒድና ዐቂዳችንን ከሚያጎድላቸው ነገር መጠበቅ እንደሚገባ ፤
- ሽርካዊ ማነብነቦችን፣ ሂርዝና መስተፋቅርን መጠቀም ክልክል መሆኑን ፤
- እነዚህን ሶስት ነገሮች እንደ ሰበብ አድርጎ ማመን ትንሹ ሺርክ ነው። ምክንያቱም ሰበብ ያልሆነን ነገር ሰበብ ማድረግ ነውና። ነገር ግን (ከሰበብም በላይ) በራሷ ትጠቅማለችም ትጎዳለችም ብሎ ካመነ ትልቁ ሺርክ ነው።
- ክልክል የሆኑ ሺርካዊ ሰበቦችን መፈፀም መከልከሉን ፤
- ሸሪዐዊ ከሆነው ሩቃ በስተቀር ማነብነብ ሺርክ ስለሆነ መከልከሉን ፤
- ቀልብ በአላህ ላይ ብቻ ነው ሊንጠለጠል የሚገባው ፤ ጉዳትም ይሁን ጥቅም የሚገኘው አጋር ከሌለው ከሱ ብቻ ነውና። ከአላህ ውጪ መልካምን የሚያመጣ የለም ፤ ከአላህ ውጪ መጥፎን የሚከላከልም የለም።
- የሚፈቀደው ሩቃ ሶስት መስፈርቶችን ያካተተ መሆን ይገባዋል: 1- ሩቃው ሰበብ ብቻ እንደሆነና ከአላህ ፍቃድ ውጪ እንደማይጠቅም ማመን፤ 2 - ሩቃው በቁርአን፣ በአላህ ስሞችና ባህሪያት ፣ በነቢያዊ ዱዓዎች፣ ሸሪዐውን በጠበቁ ዱዓዎች ሊሆን ይገባዋል፤ 3 - ሩቃው በግልፅ ቋንቋ ሊሆን ይገባል። የማይገቡ በሆኑ ቋንቋ የሚሰመሩ መስመሮችና ማታለያዎችን የራቀ ሊሆን ይገባል።