- አቡበክር ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ያላቸውን በላጭነት፤ ከሶሓቦችም ሁሉ በላጩ እርሳቸው መሆናቸውን፤ ከረሱል ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም በኋላ በርሳቸው የመሪነት ቦታ ለመተካት ይበልጥ የተገቡትም እርሳቸው መሆናቸውን፤
- በመቃብር ላይ መስገጃ መገንባት ያለፉት ህዝቦች ከሚፈፅሟቸው ውግዝ ተግባራት መካከል መሆኑ፤
- ወደ ሽርክ ሊያደርስ ስለሚችል መቃብርን የአምልኮ ስፍራ አድርጎ መያዝ፣ በውስጧም ሆነ ወደሷ ዞሮ መስገድ፣ ወይም በላያቸው ላይ መስገጃ ወይም ጉልላት መስራት ክልክል መሆኑ፤
- ወደ ሽርክ ሊያደርስ ስለሚችል በፃድቃን ላይ ድንበር ከማለፍ መጠንቀቅን፤
- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከመሞታቸው አምስት ቀናት ቀደም ብለው ማስጠንቀቃቸው ያስጠነቀቁት ጉዳይ ያለውን አሳሳቢነት እንደሚያሳይ እንረዳለን።