ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' አትበሉ።...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛውንም ሙስሊም በንግግሩ "አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)" ከማለት ከለከሉ። ወይም "አላህና እከሌ ሽተውት (ፈልገውት)" ከማለት ከለከሉ። ይህም የሆነው የአላ...
ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በናንተ ላይ ከምፈራው ነገር እጅግ አስፈሪው ትንሹ ሺ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ላይ እጅግ የሚፈሩት ነገር ትንሹን ሺርክ እንደሆነ እሱም ይዩልኝ እንደሆነ ተናገሩ። ይሀውም ለሰዎች ብሎ መስራቱ ነው። ቀጥለውም ለይዩልኝ የሚሰሩ ሰዎች የትንሳኤ ቀን የሚ...
ከአቡዘር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል: "አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሌላ ሰው "አንተ አመፀኛ" ወይም "አንተ ከሃዲ" ያለ ሰው ያ ሰው እንደተናገረው ካልሆነና ለተጠቀሰው ባህሪ የተገባ ካልሆነ ንግግሩ ወደራሱ የሚመለስ መሆኑን...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በሰዎች ውስጥ ሁለ...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሰዎች መካከል ስለሚገኙ ሁለት የከሃዲያን ስራዎችና የድንቁርና ዘመን ስነ ምግባሮች ተናገሩ። እነርሱም: የመጀመሪያው: ሰዎችን በዘራቸው መተቸት፣ ማሳነስ...
ከአቡ መርሠድ አልጘነዊይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መቃብሮች ላይ ከመቀመጥ ከለከሉ። ይህም ወደ መቃብሮች ከመስገድ እንደከለከሉት ነው። ቀብሩ ወደ ሰጋጁ ቂብላ አቅጣጫ መሆኑን ይመስል ማለት ነው። ይህም የተከለከለው ወደ ሺርክ ከሚያዳርሱ ምክንያቶች አንዱ...

ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' አትበሉ። ይልቁንም 'አላህ ከሻ (ከፈለገ) ከዚያም እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' በሉ።"

ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በናንተ ላይ ከምፈራው ነገር እጅግ አስፈሪው ትንሹ ሺርክ ነው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ትንሹ ሺርክ ምንድነው?" ብለው ጠየቁ። እሳቸውም "ይዩልኝ ነው። የትንሳኤ ቀን ሰዎች በስራዎቻቸው የተመነዱ ጊዜ ለነርሱ አሸናፊውና የላቀው አላህ እንዲህ ይላቸዋል፦ 'እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ?' "

ከአቡዘር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል: "አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በሰዎች ውስጥ ሁለት ነገሮች አሉ፤ ክህደት ናቸው። በዘር መተቸትና በሞተ ላይ ሙሾ ማውረድ ናቸው።"»

ከአቡ መርሠድ አልጘነዊይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"

ከአቡ ጦልሓ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መላዕክቶች ውሻና ስዕል ወዳለበት ቤት አይገቡም።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መላእክት ውሻ እና ቃጭል ካላቸው መንገደኞች ጋር አብረው (አይጎዳኙም) አይሄዱም።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ሰይጣን አንዳችሁ ዘንድ በመምጣት "ይህን የፈጠረው ማነው? ይህንንስ የፈጠረው?" እያለ ይጠይቃችኋል "ጌታህንስ የፈጠረው ማነው?" ብሎ እስኪጠይቃችሁ ድረስ ይደርሳል፤ ይህ ጥያቄ የደረሰው ጊዜ በአላህ ይጠበቅም ይከልከልም።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም። ባሪያዬ ወደ እኔ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የምወደው ቢሆን እንጂ፤ የወደድኩትም ጊዜ የሚሰማበት መስሚያው እሆነዋለሁ፣ የሚያይበት መመልከቻ እሆነዋለሁ፣ የሚጨብጥበት እጅ እሆነዋለሁ፣ የሚራመድበት እግር እሆነዋለሁ፣ ቢጠይቀኝ እሰጠዋለሁ፣ ከኔ ጥበቃ ከፈለገ እጠብቀዋለሁ። እኔ ከማደርገው መካከል የሙእሚን ነፍስን ለመውሰድ እንደማመነታው በአንዳችም ነገር አላመነታሁም። እርሱ ሞትን ይጠላል እኔ ደግሞ እርሱን መጉዳት እጠላለሁ።›'"

ከዒርባድ ቢን ሳሪያህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና በርሷ ምክንያት ልቦናዎች የራዱበት፣ ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰን ምክር መከሩን። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! የመከሩን ምክር የተሰናባች ምክር ሆኖብናልና ለእኛ የሚሰጡን አደራ አለን?' ተባሉ። እርሳቸውም ' አላህን በመፍራት፤ የሐበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን (መሪያችሁ) እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። ከኔ በኋላ ከባድ ልዩነትን ታያላችሁ፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።' አሏቸው።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ከመሪ ትእዛዝ አምፆ በመውጣት የሙስሊሙን ህብረት ተለይቶ የሞተ የድንቁርና አሟሟት ሙቷል። ለወገኑ ሲል እየተቆጣ ወይም ወደ ወገንተኝነት እየተጣራ ወይም ወገን ለይቶ እየረዳ በዕውር ባንዲራ ስር እየተዋጋ ቢገደል የድንቁርና አሟሟት ሙቷል። በኡመቴ ላይ (ሊመራ) የወጣ መልካሙንም መጥፎውንም የሚማታ ስለአማኙ ህዝብ ምንም ደንታ የሌለው የቃል ኪዳን ባለቤት ለሆኑትም በቃል ኪዳኑ የማይሞላ ሰው ከኔም አይደለም እኔም ከርሱ አይደለሁም።"

ከመዕቂል ቢን የሳር አልሙዘኒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: እኔ የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።"