- የአደን ውሻ ወይም የከብት ጠባቂ የሆነ ውሻ ወይም የአዝርዕት ጠባቂ የሆነ ውሻ ካልሆነ በቀር ውሻን ማሳደግ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
- ስዕል ማስቀመጥ መላዕክት የሚሸሹት ከሆኑ ቆሻሻ ጉዳዮች አንዱ ነው። በአንድ ስፍራ ስዕል መኖሩ እዝነትን እንድንነፈግ ምክንያት ይሆነናል። ውሻም ልክ እንደዚሁ ነው።
- ውሻ ወይም ስዕል ያለበት ቤት ውስጥ የማይገቡት መላዕክቶች የእዝነት መላዕክቶች ናቸው እንጂ ስራን የሚመዘግቡና ሌሎች እንደ መልዐከ ሞት የመሰሉ የስራ ድርሻ ያላቸው መላዕክቶች ግን ሁሉም ቤት ይገባሉ።
- ግድግዳና ሌሎች ነገሮች ላይ ነፍስ ያላቸውን ፍጡራን ስዕላቸውን ማንጠልጠል ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
- ኸጧቢ እንዲህ ብለዋል: «መላዕክት ውሻ ወይም ስዕል ያለበት ቤት የማይገቡት ማስቀመጡ ክልክል የሆኑ ውሻዎችንና ስዕሎችን ነው። ክልክል ያልሆኑ የአደን ውሻ፣ የአዝርዕትና ከብቶች ጠባቂ የሆኑ ውሻዎችን እንዲሁም ምንጣፍ ላይ፣ ትራስ ላይና የመሳሰሉት ግን በነርሱ ምክንያት መላዕክት ከመግባት አይቆጠቡም።