- ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጌታቸው ከሚዘግቡት ሐዲሥ አንዱ ነው። "ሐዲሠል ቁድስ" ወይም "ሓዲሠል ኢላሂይ" በመባል ይጠራል። እርሱም ቃሉም ሆነ መልዕክቱ ከአላህ የሆነ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌላው የተለየበት የሆኑ መለዮዎች የሉትም። ለምሳሌ: ሲያነብ በየፊደላቱ አጅር ማስገኘቱ፣ እርሱን ለማንበብ ዉዱእ ማድረግ፣ ከቻሉ አምሳያውን እንዲያመጡ የተሞገተበት መሆን፣ የቃል አወቃቀሩ መለኮታዊነትና ከዚህም ውጪ ያሉ የቁርአን መለዮዎች የሉትም ማለት ነው።
- የአላህን ወዳጆች ከማወክ መከልከሉ፤ እነርሱን በመውደድና ደረጃቸውን በማወቅ ላይም መነሳሳቱን እንረዳለን።
- የአላህን ጠላቶችን በመጣላት ላይ መታዘዙንና እነርሱን መወዳጀት መከልከሉን እንረዳለን።
- የአላህን ሸሪዓ ሳይከተል የአላህን ወዳጅነት የሞገተ ሰው በሙግቱ ውሸታም መሆኑን እንረዳለን።
- የአላህ ወዳጅነት ግዴታዎችን በመፈፀምና ክልክሎችን በመተው ነው የሚገኘው።
- ለአንድ ባሪያ የአላህን ውዴታና የዱዓን ተቀባይነት ከሚያስተርፉ ምክንያቶች መካከል ግዴታዎችን ከፈፀሙና ክልክሎችን ከተዉ በኋላ ትርፍ ስራዎችን መስራት ነው።
- የወሊዮች ልቅናና የደረጃቸው ከፍታ መጠቆሙን እንረዳለን።