- ሱናን አጥብቆ መያዝና ሱናን መከተል አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
- ለምክሮችና ልቦችን ለሚያለሰልሱ ነገሮች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ እንረዳለን።
- ከርሳቸው በኋላ ያሉት አራቱ የተመሩ ቅን ምትኮቻቸውን መከተል መታዘዙን እንረዳለን። እነሱም አቡ በከር፣ ዑመር፣ ዑሥማንና ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ናቸው።
- በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር መፍጠር መከልከሉንና ሁሉም መጤ ነገር ጥመት መሆኑንም እንረዳለን።
- የአማኞችን ጉዳይ እንዲመራ ለተሾመ ሰው ከወንጀል ውጪ በሆኑ ጉዳዮች እርሱን መስማትና መታዘዝ እንደሚገባ እንረዳለን።
- አላህን በሁሉም ወቅትና ሁኔታ የመፍራትን አንገብጋቢነት እንረዳለን።
- በዚህ ኡመት ውስጥ ልዩነት ይከሰታል። በሚከሰት ወቅት ግን ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሱና እና ወደ ቅን ምትኮቻቸው ሱና መመለስ ግድ ይላል።