ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እንዲህ በማለት ወደ ጀነት...
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አላህ ጀነትና እሳትን እነደፈጠራቸው ለጂብሪል ዐለይሂ ሰላም እንዲህ እንዳለ ተናገሩ። "ወደጀነት ሂድና ወደርሷ ተመልከት!" ጂብሪልም ሄዶ ወደርሷ ተመልክቶ ተመለሰ። ጂብሪልም እንዲህ አ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።" "የአላህ መልክተኛ...
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የዱንያ እሳት ከሰባ የጀሀነም እሳት ክፍል አንዷ ክፍል መሆኗን ተናገሩ። የአኺራ እሳት ከዱንያ እሳት በስልሳ ዘጠኝ እጥፍ የማቃጠል ደረጃዋ ይበልጣል። እያንዳንዱ የጀሀነም ክፍል ከዱንያ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን አላህ ምድርን እንደሚጨብጥና እንደሚሰበስባት፤ ሰማይንም ከፊሉን ከከፊሉ በላይ አድርጎ በቀኝ እጁ እንደሚጠቀልልና ገፍፎ እንደሚያጠፋቸው ከዚያም "እኔ ነኝ ንጉስ! የምድ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "እቃ ክፍሌን (የተንቀሳቃሽ እንስሳ) ምስል ባለበት መጋረጃ ሸፍኜው ሳለ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤታቸው ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድ ሲገቡ እቃ የምታስቀምጥበትን ትንሽዬ ክፍል ነፍስ ያላቸው ምስሎች ባለበት መጋረጃ ሸፍናው አገኟት። የ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ። በናንተ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመርየም ልጅ ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሰዎች መካከል በነቢያችን ድንጋጌ በፍትህ ሊፈርዱ መውረጃ ጊዜያቸው ቅርብ እንደሆነ ምለው ተናገሩ። በሚመጡ ወቅትም ክርስቲ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እንዲህ በማለት ወደ ጀነት ላከው። "ወደ ርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" ወደ እርሷ ተመልክቶ በመመለስ እንዲህ አለ፦ "በልቅናህ ይሁንብኝ ስለርሷ ማንኛውም ሰው ቢሰማ ከመግባት ወደኋላ የሚል የለም" አላህም በሷ ጉዳይ ትእዛዙን አስተላልፎ (ለነፍስ) በሚከብዱ ነገሮች ተከበበች። በድጋሚ ጂብሪልን "ወደርሷ ሂድና ወደርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" አለው። ወደርሷ ተመለከተ፥ ድንገት (ለነፍስ) በሚከብዱ ነገሮች ተከባ ተመለከታት። "በልቅናህ እምላለሁ! በርግጥም ማንም አይገባትም ብዬ ፈራሁ።" ብሎ ለአላህ መለሰ። አላህም፦ " ወደ እሳትና ለባለቤቶቿ በውስጧ ያዘጋጀሁትን ሂድና ተመልከት" በማለት አዘዘው። ጂብሪልም ወደርሷ ሲመለከት ያንጊዜ እሷ ከፊሏ ከፊሉን ሲበላ ተመለከተ። በመመለስም እንዲህ አለ "በልቅናህ እምላለሁ ማንም አይገባትም" አላህም በሷ ጉዳይ ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች እንድትከበብ አዘዘ። ቀጥሎም ደግመህ ወደርሷ ሂድና ተመልከት አለው ድንገት ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች ተከባ ወደርሷ ተመለከተ። "በልቅናህ እምላለሁ! ወደርሷ አንድም ከሷ አይድንም ይገባታል ብዬ ፈራሁ።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የምድር እሳት ለቅጣት) በቂ ነበረች’እኮ" ተባሉ። እሳቸውም፦ "የጀሀነም እሳት ከምድር እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጋለች። ሁሉም ክፍል የምድር እሳት አምሳያ ሀሩርነት (አቃጣይነት) ነው ያላቸው።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'"

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "እቃ ክፍሌን (የተንቀሳቃሽ እንስሳ) ምስል ባለበት መጋረጃ ሸፍኜው ሳለ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኔ ዘንድ መጡ። የተመለከቱት ጊዜም ፊታቸው ተለዋውጦ ቀደዱትና እንዲህም አሉ 'ዓኢሻ ሆይ! የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት እነዚያ በአላህ ፍጥረት የሚፎካከሩት ናቸው።'" ዓኢሻም እንዲህ አለች "ቆርጠነው በርሱ አንድ ትራስ ወይም ሁለት ትራስ አደረግንበት።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ። በናንተ ውስጥ የመርየም ልጅ ፍትሃዊ ዳኛ በቅርቡ ሆኖ ይወርዳል። መስቀልን ይሰባብራል፣ አሳማን ይገድላል፣ ግብርን ያነሳል፣ አንድም ሰው እስከማይቀበለው ድረስም ገንዘብ (ሀብት) ይበዛ።"

አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለአጎታቸው እንዲህ አሏቸው፦ " ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ" አቡ ጣሊብም "የቁረይሾች ማነወር ባልነበር "ለመስለም ያነሳሳው የሞት ፍራቻ ነው" ይላሉ ብዬ ባልሰጋ (እሰልም ነበር)" (ይህ ስጋት ባልነበር) ላ ኢላሀ ኢለላህ በማለት ደስታን አሰርፅልህ ነበር።" አላቸው። አላህም ይህን አንቀፅ አወረደ {አንተ የወደድከውን ሰው ፈፅሞ አታቀናም። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።} [አልቀሶስ: 56]

ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የሐውዴ ( ኩሬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ፣ የብርጭቆዎቹ ብዛት የሰማያት ኮኮቦች ያህል ናቸው። ከሷ አንዴ የጠጣ ከቶም መቼም አይጠማም።"

አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል። ተጣሪም እንዲህ በማለት ይጣራል: "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ቀጥሎ ተጣሪው እንዲህ በማለት ይጣራል "የእሳት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ይታረዳል ቀጥሎ እንዲህ ይላቸዋል "የጀነት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም። የእሳት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም።" ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን፦ {እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭቱን ቀን አስፈራራቸው።} [መርየም: 39] የሚለውን አንቀፅ አነበቡ። "እነዚህ በዱንያ ዝንጋቴ ውስጥ ናቸው።" {እነሱም የማያምኑ ናቸው።} [መርየም: 39]"

ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማ: "በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።"

ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "የሚጋልብ ሰው በእግረኛ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ በተቀማጭ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'"

ከአቢ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ካለውና ከጠራው አላህ ባወሩት (ሐዲሠል ቁድሲይ) አላህ እንዲህ ብሏል: "ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በነፍሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ! በመካከላችሁም እርም አድርጌዋለሁ! ስለሆነም አትበዳደሉ! ባሮቼ ሆይ! ከመራሁት በስተቀር ሁላችሁም ጠማማ ናችሁና ምራቻን ከኔ ጠይቁ እመራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! ካበላሁት በስተቀር ሁላችሁም ረሀብተኞች ናችሁና መብልን ከኔ ጠይቁ እመግባችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እኔ ካለበስኩት በስተቀር ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁና ልብስን ከኔ ጠይቁ አለብሳችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ በሌሊትም ሆነ በቀን ትሳሳታላችሁ። እኔ ደግሞ ሁሉንም ወንጀሎችን እምራለሁ። ስለሆነም ምህረትን ከኔ ፈልጉ እምራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ እኔን ጉዳትን ልትጎዱኝ አትችሉም። ጥቅምን ልትጠቅሙኝ ዘንድም አትችሉም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም ከናንተ መካከል እንደሚገኝ አንድ እጅግ አላህን ፈሪ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይጨምርም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም እንደ አንድ እጅግ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰው ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም በአንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ቢቆሙና ቢጠይቁኝ ለእያንዳንዱም የጠየቀኝን ብሰጠው መርፌ ባህር የገባች ጊዜ እንደምትቀንሰው ያህል ካልሆነ በቀር ይህ (መስጠቴ) እኔ ዘንድ ካለው (ሀብት) ምንም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ይህቺ ስራችሁ ናት ለናንተ አስቀምጥላችኋለሁ ከዚያም እራሷን እመነዳችኋለሁ። ምንዳውን መልካም ሆኖ ያገኘ አላህን ያመስግን ፤ ከዛ ውጪ ሆኖ ያገኘ ግን ከነፍሱ በስተቀር ማንንም እንዳይወቅስ።"