- መጥፎን ነገር በማውገዛችን ሳቢያ የሚከሰት ትልቅ ብልሽት እስከሌለ ድረስ በተመለከትነው ቅፅበት ማውገዝ እንደሚገባና ማቆየትም እንደሌለብን እንረዳለን።
- የትንሳኤ ቀን ቅጣት እንደ ወንጀሉ ትልቀት ይበላለጣል።
- ነፍስ ያላቸው ነገሮችን ምስል ማድረግ ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
- ምስል ማድረግ ከተከለከለባቸው ጥበቦች አንዱ ከአላህ አፈጣጠር ጋር መፎካከር ስለሆነ ነው። ይህም ምስል አድራጊው መፎካከር አሰበም አላሰበም እኩል ነው።
- ከጉዳዩ የተከለከለበትን ጎን ካራቅን በኋላም በርሱ መጠቀማችን ሸሪዓ ገንዘቦችን በመጠበቅ ላይ ያለውን ጉጉት ያስረዳናል።
- ነፍስ ያላቸውን ምስሎች በማንኛውም ቅርፅ ቢሆኑ እንኳ፣ ፕሮፌሽናል የሆነ ምስል ቢሆን እንኳ መፈብረክ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።