- የመመካት ትሩፋትን ፤ መመካት ሲሳይን ከሚያመጡ መንስኤዎች መካከል ትልቁ ነው ።
- መመካት ሰበቦችን ከመፈፀም ጋር አይጋጭም። ምክንያቱም እሳቸው ሲሳይ ለመፈለግ ማልዶ መውጣትና አምሽቶ መመለስ ትክክለኛውን መመካት እንደማይጣረሰው ተናግረዋልና።
- ሸሪዐ ለቀልብ ተግባራት ትኩረት መስጠቱን፤ መመካት የቀልብ ተግባር ነውና።
- በሰበብ ላይ ብቻ መንጠልጠል የዲን ጉድለት ሲሆን ሰበቦችን መተው ደግሞ የአይምሮ ጉድለት ነው።