/ የሚጋልብ ሰው በእግረኛ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ በተቀማጭ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'

የሚጋልብ ሰው በእግረኛ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ በተቀማጭ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "የሚጋልብ ሰው በእግረኛ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ በተቀማጭ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሰዎች መካከል "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ" የሚለውን ሰላምታን የማቅረብ ስነ-ስርዓትን ጠቆሙ። ህፃን በትልቅ ላይ፣ ጋላቢ በእግረኛ ላይ፣ እግረኛ በተቀማጭ ላይ፣ ጥቂት ቁጥር ያላቸው በብዙዎቹ ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።

Hadeeth benefits

  1. ሐዲሥ ላይ በመጣው መልኩ ሰላምታን ማቅረብ እንደሚወደድ እንረዳለን። ነገር ግን እግረኛ በጋላቢ ላይ ወይም ከዚህም ውጪ ሐዲሡ ላይ ከተጠቀሰው በተቃራኒው ሰላምታ ቢያቀርብ ከበላጩና ከተሻለው ተቃራኒ ቢሆንም ይፈቀዳል።
  2. በሐዲሡ ላይ በተጠቀሰው አፈፃፀም መልኩ ሰላምታን ማስፋፋት ውዴታንና ትስስርን ከሚያመጡ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
  3. በሐዲሡ ላይ ከተጠቀሱት ተመሳሳይና ተመጣጣኝ ከሆኑ የተሻለው ሰላምታውን የሚጀምረው ነው።
  4. የሰው ልጅ የሚያስፈልገውን ሁሉ በማብራራት ረገድ የሸሪዓን ምሉዕነት እንረዳለን።
  5. የሰላምታን ስነ-ስርዓት ማስተማርና ለሁሉም የሚገባውን ሐቅ (መብት) መስጠት እንደሚገባ እንረዳለን።