- ጀነትና እሳት አሁን ላይ ያሉ መሆናቸውን ማመን እንደሚገባ፤
- በሩቅ ምስጢር ነገሮች እና ከአላህና መልክተኛው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመጡ ነገሮች ሁሉ ማመን ግዴታ መሆኑን፤
- ወደጀነት የምታደርስ መንገድ ስለሆነች በአስቸጋሪ ነገሮች ላይ መታገስ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን፤
- ወደ እሳት የሚያደርስ መንገድ ስለሆነ ክልክል ነገሮችን መራቅ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን፤
- ጀነት በአስቸጋሪ ነገሮች እሳት ደግሞ ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች የተከበቡ መደረጋቸው በዱንያ ህይወት ውስጥ ፈተናዎችና ሙከራዎች እንዳሉ የሚያሲዝ ነው።
- የጀነት መንገድ አስቸጋሪና ከባድ ስለሆነ ትእግስትና ከኢማን ጋር ትኩረት ይፈልጋል። የእሳት መንገድ በዱንያ ውስጥ ለነፍስ በሚያስደስትና በሚያረካ ነገሮች የተሞላ መሆኑን እንረዳለን።