- ይህ ሐዲሥ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው ከሚዘግቡት ሐዲሦች መካከል አንዱ ነው። ሐዲሠል ቁድስ ወይም ሓዲሠል ኢላሂይ በመባልም ይጠራል። ይህም ቃሉም ሆነ መልዕክቱ ከአላህ የሆነ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌሎች የተለየበት የሆኑ የቁርአን መለዮች የሉትም። ለምሳሌ: - በማንበቡ (ሓሰና የሚያስገኝ) አምልኮን መፈፀም፣ ለሱ ጦሀራ ማድረግ ፣ የሱን አምሳያ ከቻላቹ አምጡ የተባለለት ተዓምራዊነቱና ሌሎችም ቁርአን የተለየበት መለዮዎች ይጠቀሳሉ።
- ባሮች የሚጎናፀፉት እውቀትና መመራት በአላህ መምራትና ማሳወቅ ነው።
- አንድ ባሪያ የሚያገኘው መልካም ነገር በአላህ ችሮታ ነው። የሚያገኘው መጥፎ ነገር ግን በነፍሱና በስሜቱ ሳቢያ ነው።
- መልካምን የሰራ በአላህ መግጠም ነው። የአላህ መመንዳትም ከአላህ የሆነ ችሮታ ስለሆነ ምስጋናው ለአሏህ ነው። መጥፎን የሰራ ግን ከነፍሱ በቀር ማንንም እንዳይወቅስ።