ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይ...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሰው ልጅ ፍፁም ጓደኛውንና ባልደረባውን በልማዱና ኑሮው እንደሚመሳሰል፤ ጓደኝነትም በስነምግባር፣ በባህሪና የኑሮ ዘይቤ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ገለፁ። ለዚህም ጓደኛ አመራረጣችን...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይመልከት።"

ከሙጊራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "ከኡመቴ መካከል የበላይ የሆኑ ጭፍሮች (ከመኖር) አይወገዱም። የአላህ ትእዛዝ እስኪመጣባቸው ድረስም የበላይ እንደሆኑ ይቆያሉ።"

ከተሚም አድዳሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የዚህ ሃይማኖት ጉዳይ ቀንና ምሽት የደረሰበት ስፍራ ሁሉ ይደርሳል። አላህ፤ በሀያሉ ሀይልም ይሁን በውርደታሞች ውርደት ይህንን ሃይማኖት እያንዳንዱ የግንብ (የከተማ) ቤት ውስጥም ይሁን የሳር ቤት (የገጠር ቤት) ውስጥ ሳያስገባው አይቀርም። ወይ አላህ በርሱ ኢስላምን የበላይ በሚያደርግበት ሀይል አልያም አላህ በርሱ ክህደትን በሚያዋርድበት ውርደት (ኢስላም የበላይነቱን ይጎናፀፋል)።"» ተሚም አድዳሪም እንዲህ ይል ነበር "ይህንንም በወገኖቼ አወቅኩት። ከወገኖቼ የሰለሙት መልካምን፣ ልቅናና ክብርን አገኙ። ከወገኖቼ መካከል የካዱትንም ውርደት፣ የበታችነትና ግብር አገኛቸው።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ። ልክ እንደጀመረውም ወደ እንግዳነት ይመለሳል። ለእንግዶቹ 'ጡባ' ይሰጣቸዋል (አለላቸው)።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ያ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ኡመት ውስጥ አንድም አይሁድ ይሁን ክርስቲያን ስለኔ ሰምቶ ከዚያም በዛ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት የለም። ከእሳት ጓዶች መካከል ቢሆን እንጂ"

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጀምረተል ዐቀባህ መወርወሪያ ንጋት ላይ ግመላቸው ላይ ሆነው 'ጠጠር ልቀምልኝ!' አሉኝ። ሰባት ጠጠርም ለቀምኩላቸው። እነርሱም ትናንሽ በጣት መሀል የሚወረወሩ ጠጠሮች ነበሩ። መዳፋቸው ላይ አኑረው እያገላበጧቸውም 'እንደነዚህ ልክ ወርውሩ!' አሉ። ቀጥለውም 'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።"

ዐብደሏህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፡ 'ፅንፈኞች (ወሰን አላፊዎች) ጠፉ!' ሶስት ጊዜ ደጋገሟት።"

ከዓዲይ ቢን ሓቲም እንደተላለፈው: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "አይሁዶች ቁጣ የሰፈነባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳሳቱ ናቸው።"

ዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዐስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አላህ ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት የፍጡራንን ውሳኔ ፅፏል።" እንዲህም አሉ፦ " ዐርሹ ውኃ ላይ ነው።"

ዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: እውነተኛና (ይዘውት በመጡትም ሁሉ) እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን) ነገሩን፦ "የአንዳችሁ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀንና ምሽት ይሰበሰባል። ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ የረጋ ደም ይሆናል፤ ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ ቁራጭ ስጋ ይሆናል፤ ከዚያም ወደርሱ መልዐክ ይላካል ፤ መልዐኩ አራት መልእክቶች ይታዘዛል፤ ሲሳዩን፣ የሞት ቀጠሮውን፣ ስራውንና እድለቢስ ወይም እድለኛ መሆኑን ይጻፋል። ከዚያም በውስጡ ነፍስ ይነፋበታል። አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ወሳኔ) ይቀድምና የእሳት ጉዶችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል። አንዳችሁ በርሱና በእሳት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ወሳኔ) ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።"

ኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።"

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።"