- እስልምና ከተሰራጨና ከታወቀ በኋላም እንግዳነቱ መልሶ እንደሚከሰትበት መናገራቸው፤
- ይህ ሐዲሥ ከነቢይነት ምልክቶች መካከል አንዱ ምልክት ነው። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከርሳቸው በኋላ የሚከሰተውን ተናግረው እንደተናገሩት መከሰቱ ነው።
- ሀገሩንና ዘመዶቹን ለእስልምና ብሎ የተወ ሰው ያለው ደረጃ መገለፁ፤ ለርሱም ጀነት ይሰጠዋል።
- እንግዶች ማለት: ሰዎች በተበላሹ ጊዜ የተስተካከሉና ሰዎች ያበላሹትንም የሚያስተካክሉ ናቸው።