- መልካሞችን በመወዳጀትና በመምረጥ መታዘዙን፤ መጥፎዎችን መወዳጀት ደግሞ መከልከሉን እንረዳለን።
- ከዘመድ ይልቅ ጓደኛን ብቻ ለይተው መጥቀሳቸው ጓደኛ አንተ ራስህ ነህ የምትመርጠው ስለሆነ፤ ወንድምና ቅርብ ዘመድ ግን አንተ ምንም ምርጫ ስለሌለህ ነው።
- ጓደኛን መያዝ የግድ ከማስተዋል በኋላ የመጣ መሆን አለበት።
- አንድ ሰው አማኞችን በመወዳጀት ዲኑን እንደሚያጠነክርና አመፀኞችን በመወዳጀት ደግሞ እንደሚያደክመው እንረዳለን።